Skip to main content
x

ሰሞኑን የተቀሰቀሰው ተቃውሞና እያስከተለ ያለው ጉዳት

ወጣት ሌንሳ ገመቹ ተወልዳ ያደገችው በኦሮሚያ ክልል ፊኒፊኔ ልዩ ዞን ሱሉልታ ከተማ ሲሆን፣ ወላጆቿ ሁለት ልጆች ብቻ መውለዳቸውንና እሷ የመጨረሻ ልጅ እንደሆነች ትናገራለች፡፡፡ በ1994 ዓ.ም. የአሥረኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ብትወስድም ውጤት እንዳልመጣላት ታስታውሳለች፡፡

የዞን 9 ጦማሪዎች ክስ ተቋርጦ ተሰናበቱ

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የዞን 9 ጦማሪዎች ክስ እንዲቋረጥና እንዲለቀቁ ወሰነ፡፡ ክሳቸው እንዲቋረጥ የተወሰነላቸው ናትናኤል ፈለቀ፣ በፍቃዱ ኃይሉና አጥናፍ ብርሃኔ ሲሆኑ፣ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ነበር ክስ የተመሠረተባቸው፡፡ ተከሳሾቹ ዛሬ የፍርድ ቤት ቀጠሮ የነበራቸው ሲሆን፣ ፍርድ ቤት ሲደርሱ ክሳቸው እንደተቋረጠ ተነግሯቸው ወደየቤታቸው እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በተቀሰቀሰ ተቃውሞ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

በኦሮሚያ ክልል ከሰኞ የካቲት 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ እንደ አዲስ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ የንግድና የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች በሙሉ ተገትተው ከመቆየታቸውም በላይ በሰው ሕይወትና በአካል ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ በንብረት ላይም ቀላል የማይባል ጉዳት መድረሱ ታውቋል፡፡

የቀድሞ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር በዱከም ሊያደርጉት የነበረው ጉብኝት በተፈጠረው አለመረጋጋት ሳቢያ ተሰረዘ

የቀድሞ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር በዱከም የሚገኘውን የኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን እንዲጎበኙ የተያዘላቸው ፕሮግራም፣ ከሰኞ የካቲት 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ ዙሪያና በሌሎችም የኦሮሚያ አካባቢዎች እየተካሄደ በሚገኘው ተቃውሞና አድማ ሳቢያ መሰረዙ ታወቀ፡፡

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ለየት ያሉ ውሳኔዎችን እንደሚያስተላልፍ ተጠቆመ

የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ከዚህ በፊት ከነበሩት ለየት ያሉ ውሳኔዎች እንደሚያስተላልፍ ተጠቆመ፡፡ የብአዴን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዓለምነው መኮንን፣ የክልሉን ሕዝብ ችግሮች በዘላቂነት ሊፈታ የሚያስችልና ከዚህ በፊት ይተላለፉ ከነበሩት ለየት ያሉና ጠንካራ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ቢሊየነሩ ቢል ጌትስ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ገለጹ

የዓለም ቁጥር አንድ ቢሊየነር ቢል ጌትስ በኢትዮጵያ እየታየ ያለው የፖለቲካ ቀውስ እንደሚያሳስባቸው ገለጹ፡፡ ለአገሪቱ ሕዝቦች ሰላምና ደኅንነት ሲባል ችግሩ በቶሎ ዕልባት እንዲያገኝ መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡ ቢል ጌትስ ይህንን የተናገሩት ቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በየዓመቱ ይፋ የሚያደርገውን መጽሔት በማስመልከት፣ ለአፍሪካ ጋዜጠኞች በስልክ ኮንፈረንስ ወቅት በሪፖርተር ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ነበር፡፡

ክሳቸው የተቋረጠው እነ አቶ በቀለ ገርባ ከእስር ተለቀቁ

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ከየካቲት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ክሳቸው እንዲቋረጥ ያደረገላቸው አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሰባት ተጠርጣሪዎች፣ ማክሰኞ የካቲት 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ከእስር ተለቀቁ፡፡ በተጨማሪም ከ340 በላይ ተጠርጣሪዎች ረቡዕ የካቲት 7 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደሚፈቱ ታውቋል፡፡

የአማራ ክልል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በመከላከያ ምስክርነት ተቆጠሩ

በአማራ ክልል በጎንደር ከተማና ሰሜን ጎንደር በተለያዩ ወረዳዎች ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ከግንቦት ሰባት አመራሮች ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ አመፅ በማስነሳትና በመምራት በግልና በመንግሥት ንብረት ላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው ክስ የተመሠረተባቸው እነ ንግሥት ይርጋ፣ የክልሉን ፕሬዚዳንት ጨምሮ በርካታ ባለሥልጣናትን በመከላከያ ምስክርነት ቆጠሩ፡፡

የኦሮሚያ ክልል አምስት በካይ ፋብሪካዎችን ዘጋ

ከአዲስ አበባ ዙሪያ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ በኦሮሚያ ክልል ከተሞች የሚገኙ አምስት በካይ ፋብሪካዎች መዝጋቱን የኦሮሚያ ክልል የአካባቢ ጥበቃ፣ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን በበኩሉ ከተማውንና ዙሪያውን የሚገኙ የኦሮሚያ አካባቢዎችን የሚበክሉ ፋብሪካዎችን ቢያግድም፣ ዕግዱ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ትዕዛዝ ተነስቶ፣ ተጨማሪ የዕፎይታ ጊዜ ተፈቅዶላቸዋል፡፡

በሐረር ከተማ ሐማሬሳ በተፈጠረ ግጭት አራት ሰዎች ሕወታቸውን አጡ

በሐረር ከተማ ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎችን አስጠልሎ በሚገኘው የማሬሳ መጠለያ ጣቢያ ትናንት የካቲት 4 ቀን 2010 ዓ.ም. በወጣቶችና በፀጥታ አካላት መካከል በተፈጠረ ግጭት አራት ግለሰቦች መሞታቸውና አሥር ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ታወቀ፡፡

ከሞቱት ውስጥ ሦስቱ በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ሲሆን አንዱ ደግሞ የኦሮሚያ ፖሊስ አባል መሆኑ ታውቋል፡፡