Skip to main content
x

ተጠርጣሪው የኦሮሚያ ባለሥልጣን ከግለሰቦች ከ10.5 ሚሊዮን ብር ጉቦ መቀበላቸው ተገለጸ

የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለሥልጣን አቶ ወንድሙ ቢራቱን በተጠረጠሩበት ከባድ የሙስና ወንጀል በቁጥጥር ሥር አውሎ እየመረመራቸው የሚገኘው የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን፣ ሰሞኑን ባካሄደው ምርመራ ተጠርጣሪው ከግለሰቦች 10.5 ሚሊዮን ብር ጉቦ የተቀበሉበትን ሰነድ መሰብሰቡን ገለጸ፡፡

በጋምቤላ ክልል ከ126 በላይ የሌላ ብሔር ተወላጆችን በመግደል የተጠረጠሩ 45 ሰዎች ተከሰሱ

በጋምቤላ ክልል በማጃንግ ዞን በተለይ በመንገሽና በሶደሬ ወረዳዎች በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች፣ ከተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ወደ ክልሉ በመሄድ ለበርካታ ዓመታት በሕጋዊ መንገድ ይኖሩ የነበሩ ከ126 በላይ የተለያዩ ብሔር ተወላጆችን፣ ጭካኔ በተመላበት ሁኔታ በግፍ በመግደል የተጠረጠሩ 45 የክልሉ ተወላጆች ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

የታገዱት የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አመራሮች በአዲስ ተተኩ

የኦሮሚያ የኅብረት ሥራ ባንክ ፕሬዚዳንት፣ ሁለት ምክትል ፕሬዚዳንቶችና የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር፣ ምክትል የቦርድ ሊቀመንበርና የዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎት ኃላፊ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሰሞኑን ከኃላፊነታቸው ከታገዱ በኋላ፣ ያልታገደው ቀሪው ቦርድ ባንኩን የሚመሩ አዳዲስ አመራሮችን ሰየመ፡፡

የፓርላማ ተመራጩ አምባሳደር ዶ/ር አዲስ ዓለም ባሌማ የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ

የትግራይ ክልል ምክር ቤት የሕወሓት ሊቀመንበር አቶ ኣባይ ወልዱ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲቀጥሉ ሲወሰን፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆነው የተመረጡት አምባሳደር ዶ/ር አዲስ ዓለም ባሌማን ምክትላቸው አድርጎ ሾሟል፡፡

ኢንጂነር ይልቃል ካቢኔያቸውን እንደ አዲስ አዋቀሩ

ከነሐሴ 16 እስከ ነሐሴ 17 ቀን 2007 ዓ.ም. ለመጀመርያ ጊዜ በተካሄደው የሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ ፓርቲውን ለመጪዎቹ ሦስት ዓመታት በፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ በድጋሚ የተመረጡት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ ያዋቀሩትን አዲስ ካቢኔ መስከረም 9 ቀን 2008 ዓ.ም. ለብሔራዊ ምክር ቤቱ አቅርበው አፀደቁ፡፡

‹‹በርካታ ሮቢንሰኖችና ፎርዶች ግንኙነታችንን እንደሚያበረቱት ተስፋ አለኝ››

ዴቪድ ኬኔዲ፣ በአሜሪካ ኤምባሲ የፐብሊክ አፌርስ ኃላፊ እየተገባደደ ባለው የ2015 ዓመት (እ.ኤ.አ.) የአሜሪካ  የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ላለፉት 75 ዓመታት አሜሪካ በመላው ዓለም ስትተገብራቸው የቆዩትን የልምድ ልውውጥ ፕሮግራሞች በመዘከር ላይ ይገኛል፡፡

‹‹የመንግሥት አመራር በሙሉ ሙስና ስለፈጸመ ስብስብ አድርጋችሁ የምታደርጉትን አድርጉ የሚል መልዕክት አልደረሰኝም››

  አቶ ዓሊ ሱሌይማን፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽነር ባለፈው ዓርብ መስከረም 7 ቀን 2008 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽነር አቶ ዓሊ ሱሌይማን፣ ከጋዜጠኞች ከተነሱላቸው ጥያቄዎች መካከል አንዱ መንግሥታዊው ሥርዓት በሙስና ውስጥ መዘፈቁን በግልጽ እየተናገረ፣ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ግን በመናኛ ጉዳዮች ላይ አተኩሯል የሚል ነው፡፡