Skip to main content
x

በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር አካባቢ በተከሰተ ግጭት ምክንያት የሰዎች ሕይወት አለፈ

በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር መተማ ወረዳ በእርሻ መሬት ይገባኛል ምክንያት ተከስቶ በነበረው ግጭት የሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ ግጭቱ በመከላከያ ኃይል ጣልቃ ገብነት ቢቆምም፣ ግጭቱን ለዘለቄታው ለመፍታት እንዲያስችል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ለሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሐሰን አል በሽር የላኩትን መልዕክት አድርሰዋል፡፡

መንግሥት ያቀረበው የምሕረት መስጫ አዋጅ ሳይፀድቅ ፓርላማው ለእረፍት ተበተነ

በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው ለተያዙ፣ ለተፈረደባቸውና ሳይያዙ በውጭ አገር በስደት ለሚኖሩ ግለሰቦችና የሕግ ሰውነት ላላቸው አካላት ምሕረት ለመስጠት መንግሥት ያቀረበው የምሕረት መስጫ አዋጅ ሳይፀድቅ፣ ፓርላማው የዓመቱን የሥራ ጊዜውን አጠናቆ ለእረፍት ተበተነ፡፡

ዶ/ር መረራ ጉዲና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ቦርድ አባል ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሰየሙ

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የተጓደሉ ቦርድ አባላት እንዲሟሉ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መረራ ጉዲናን (ዶ/ር) የቦርድ አባል፣ እንዲሁም የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትሩን አቶ አህመድ ሺዴ ደግሞ የቦርድ ሰብሳቢ አድርገው ሰየሙ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶ/ር መረራ ጉዲናን የኢቢሲ ቦርድ አባል አድርገው ሰየሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሐሙስ ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ.ም. በርሳቸው ተፈርሞ በወጣ ደብዳቤ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር መረራ ጉዲናን (ዶ/ር) ከሌሎች ሦስት ግለሰቦች ጋር የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቦርድ አባል አድርገው ሰየሙ፡፡

የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪና የሐዋሳ ከንቲባ ሥልጣናቸውን ለቀቁ

በቅርቡ በደቡብ ክልል በሐዋሳ ከተማ በነበረው ግጭት ምክንያት የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ አዱላና የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ፡፡ ከሦስት ሳምንታት በፊት በተከሰተው ግጭት አሥር ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው 80 ሰዎች የተጎዱ ሲሆን፣ 3500 ደግሞ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፡፡

ካሁን ቀደም በሐዋሳው ጥቃት በወላይታ ተወላጆች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ነው በማለት ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡ ሰዎች በተቀሰቀሰ ሁከት ምክንያት፣ አምስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ሥልጣናቸውን መልቀቃቸው ይታወሳል፡፡

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሦስት የማረሚያ ቤቶች አመራሮችን ከኃላፊነታቸው አነሳ

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሦስት የማረሚያ ቤት አመራሮችን ከኃላፊነታቸው አንስቶ በምትካቸው አዳዲስ አመራሮችን ሾመ፡፡ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ከኃላፊነታቸው ያነሳቸው የማረሚያ ቤቶች ዋና ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ረጋሳ፣ የሰው ሀብትና መሠረታዊ ፍላጎት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጌትዬ ደጀኔና የጥበቃና ተሃድሶ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ወልደ ሩፋኤል ናቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሽብርተኝነት የተፈረጁ ድርጅቶችን ፍረጃ ለማስነሳትና ምሕረት ለማሰጠት በፓርላማ እንደሚገኙ ታወቀ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጁ ድርጅቶች ፍረጃው ተነስቶላቸው በነፃነት መንቀሳቀስ እንዲችሉና ለአገራዊ መግባባት ሲባል በወንጀል ለሚፈለጉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ምሕረት እንዲደረግላቸው ባሳለፋቸው ውሳኔዎች ላይ፣ ፓርላማው ሐሙስ ሰኔ 28 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደሚወያይና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ተገኝተው ማብራሪያ እንደሚሰጡ ታወቀ።

በውጭ ያሉ ተቃዋሚዎችን ወደ አገር ውስጥ እያስገባ ያለው የሰላም ጥሪ

ኢትዮጵያ ላለፉት ሦስት ዓመታት በከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞና አመፅ ስትታመስ ቆይታ አንፃራዊ የሚባል ሰላምና መረጋጋት የታየበት ወቅት ላይ ትገኛለች፡፡ ምንም እንኳን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ግጭቶች እየተከሰቱና የሰዎች ሕይወት እያለፈ፣ አካል እየጎደለና ንብረት እየወደመ ቢሆንም፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ከመጡ ጊዜ በኋላ አንፃራዊ ሰላምና መረጋጋት በአገሪቱ ታይቷል፡፡