Skip to main content
x

የፓርላማው ግብረ ኃይል የተከሰቱ ግጭቶችን መንስዔ በተመለከተ ያጠናቀረውን ሪፖርት ሊያቀርብ ነው

በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የተከሰቱና ያልተፈቱ ግጭቶች መነሻ ምክንያት እንዲመረምር በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተቋቁሞ የተሰማራው ግብረ ኃይል፣ ተልዕኮውን አከናውኖ ያጠናቀረውን ሪፖርት ሊያቀርብ ነው።

ከቂሊንጦ ቃጠሎ ጋር በተገናኘ የምስክሮች አቀራረብ መዘግየት ተቃውሞ አስነሳ

በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቂሊንጦ እስረኞች ማቆያ ቤት ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም. በመቃጠሉ የ23 እስረኞች ሕይወት ካለፈ በኋላ ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባሉ 38 ተጠርጣሪዎች ተከሰው፣ ዓቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ የቆጠራቸውን ምስክሮች እያቀረበ ነው፡፡ በምስክሮቹ አቀራረብ መዘግየት ምክንያት  ተከሳሾቹ ሰኞ ታኅሳስ 23 ቀን 2010 ዓ.ም. ተቃውሟቸውን ለፍርድ ቤት አቅርበዋል፡፡

ትምባሆ ድርጅትን ከገዛው የጃፓን ኩባንያ ጋር ምክክር ሳይደረግ በሲጋራ ላይ የታሰበው ከፍተኛ ታክስ እንዳይጣል ትዕዛዝ ተሰጠ

ብሔራዊ ትምባሆ ድርጅትን በከፍተኛ ዋጋ ከገዛው የጃፓን ኩባንያ ጋር ምክክር ሳይደረግ በሲጋራ ምርቶች ላይ ታክስ እንዳይጣል፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ትዕዛዝ ማስተላለፉን የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡

የመኢአድና የሰማያዊ አመራሮች የሰሜን አሜሪካ ቆይታቸው ውጤታማ እንደነበር አስታወቁ

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) ባደረገላቸው ጥሪ መሠረት በሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች ያደረጉት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውጤታማ እንደነበር፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ሊቀመንበር በዛብህ ደምሴ (ዶ/ር) እና የሰማያዊ ፓርቲ (ሰማያዊ) ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ አስታወቁ፡፡

ከ8.2 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ ስምንት ተከሳሾች በነፃ ተሰናበቱ

የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ለሕዝብ ውኃ ለማቅረብ በውጭ ምንዛሪ ያስገባቸውን ከ8.2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው 120 ዓይነት የቧንቧ ዕቃዎች፣ በሕገወጥ መንገድ በመውሰድ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው ተከሰው ከነበሩት አሥር ተጠርጣሪዎች ውስጥ ስምንቱ በነፃ ተሰናበቱ፡፡

የዓቃቤ ሕግ ቁሳዊ ማስረጃዎቹን ለዶ/ር መረራ ጉዲና እንዲሰጣቸው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጠ

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት የፌዴራል ዋና ዓቃቤ ሕግ በማስረጃነት ያቀረባቸው የቪዲዮ፣ የድምፅና የፎቶግራፍ ማስረጃዎች ይሰጡኝ በማለት ለጠየቁት ዶ/ር መረራ ጉዲና ማስረጃዎች እንዲሰጣቸው ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

የፓርላማው አዳዲስ ጅምሮችና አንድምታዎች

በሥራ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፓርላማ አባላት ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ በሚከተለው የዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት የዲሲፕሊን (ሥነ ሥርዓት) መመርያ ምክንያት፣ ከሥራ አስፈጻሚው የመንግሥት አካል ጋር የፖሊሲ ክርክር ውስጥ እንዲገቡ አይፈቀድላቸውም፡፡

ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው በባቢሌ መጠለያ ካምፕ ውስጥ ያሉ ተፈናቃዮች የከፋ ችግር ውስጥ ነን አሉ

ከ2010 ዓ.ም. መግቢያ ጀምሮ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በተቀሰቀሱ ግጭቶች ሳቢያ፣ ከኦሮሚያ ክልል በመፈናቀል በባቢሌ መጠለያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ የሶማሌ ክልል ተወላጆች የከፋ ችግር ውስጥ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች የፖለቲካ ትግል ማድረጊያ መሣሪያዎች መሆናቸውን የመንግሥት ሪፖርት አመለከተ

ዩኒቨርሲቲዎች ከመማር ማስተማርና ችግር ፈቺ የጥናትና የምርምር ሥራዎችን ከማከናወን ይልቅ፣ የፖለቲካ ትግል ማድረጊያ መሣሪያዎች እየሆኑ መምጣታቸውን በመንግሥት የተዘጋጀ ሪፖርት አመለከተ፡፡

የፌዴራል መንግሥት በውክልና የወሰደውን የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለሥልጣን መልሶ አስረከበ

የፌዴራል መንግሥት በውክልና ተረክቦ ያስተዳድር የነበረውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለሥልጣን መልሶ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስረከበ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው ረቡዕ ታኅሳስ 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ከአምስት ዓመታት በላይ ተለይቶ የቆየውን የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ባለሥልጣንን፣ ከኢትዮጵያ ጉምሩክና ገቢዎች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሞገስ ባልቻ ተረክበዋል፡፡