Skip to main content
x

መንግሥት ከድርቅ ይልቅ በኮሙዩኒኬሽን ቀውስ መቸገሩን አስታወቀ

በአገሪቱ ተከስቶ የነበረውን ቀውስ መቋቋም ቢቻልም መንግሥት በኮሙዩኒኬሽን ቀውስ መቸገሩን አስታወቀ፡፡ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ  (ዶ/ር) ዓርብ ጥር 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ እንደተናገሩት፣ ተከስቶ የነበረውን ድርቅ መቋቋም ቢቻልም እንኳ፣ አገሪቷ በኮሙዩኒኬሽን ቀውስ ሳቢያ ተቸግራለች፡፡ በድርቅ ምክንያት ያጋጠሙ ችግሮችን መንግሥት በብቃት እየተወጣ ነው ብለዋል፡፡

የድሮን መመርያ እየተዘጋጀ ነው

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን እያደገ የመጣውን የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር የሚያስችል፣ የድሮን መመርያ በማዘጋጀት ላይ እንደሆነ አስታወቀ፡፡ የድሮን ቴክኖሎጂ አዲስ በመሆኑ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ አገሮች የድሮን ሕግ የላቸውም፡፡ ድሮኖች አነስተኛና በቀላል ዋጋ የሚገዙ በመሆናቸው በማንኛውም ግለሰብ እጅ እየገቡ ነው፡፡ ድሮን ለስለላ፣ ለውጊያ፣ ለቅኝት ፎቶግራፍና ለቪዲዮ ቀረፃ፣ ለመድኃኒትና የሕክምና አገልግሎቶች አቅርቦትና ለመሳሰሉት አገልግሎቶች ይውላል፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን 153.9 ሚሊዮን ብር እንዳይከፈለው ክስ ቀረበበት

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በኦሮሚያ ክልል የጌዶ-ፊንጫ-ለምለም በረሃ መንገድ ፕሮጀክት የጌዶ መናቤኛ መንገድ ሥራ ለማሠራት፣ ሀውክ ኢንተርናሽናል የፋይናንስና ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ጋር በነበረው የሥራ ውል ምክንያት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ቀረበበት፡፡ ባለሥልጣኑን የከሰሰው ሀውክ ኢንተርናሽናል ፋይናንስና ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በክሱ እንዳብራራው፣ ለመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና ንብ ባንክ 153,957,947 ብር አስይዟል፡፡

የአማራ ክልል በወልዲያና አካባቢው በነበሩ ግጭቶች 15 ሰዎች እንደሞቱ ገለጸ

የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ጥር 26 ቀን 2010 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ በወልዲያ፣ በቆቦና በመርሳ ከተሞች በነበረው ግጭት የ13 ንፁኃን ዜጐችና የሁለትፀጥታ ኃይል አባላት በድምሩ 15 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ገለጸ፡፡

የአፍሪካን ችግሮች ለመፍታት ቁርጥ ያሉ ውሳኔዎች ያልተላለፉበት 30ኛው የመሪዎች ጉባዔ

30ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ጥር 20 እና 21 ቀን 2010 ዓ.ም. በኅብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡ በአሁኑ የመሪዎች ጉባዔ የፀረ ሙስና ዘመቻ፣ የአፍሪካ ኅብረት ማሻሻያ፣ ነፃ የንግድ ቀጣና መመሥረት፣ የአፍሪካን የአየር ክልል ለአፍሪካ አየር መንገዶች ነፃ ማድረግና በአኅጉሪቱ በሚታዩ የፀጥታ ሥጋቶችና ሌሎች አጀንዳዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ ባለፈው እሑድና ሰኞ በተካሄደው 30ኛው የመሪዎች ጉባዔ የአርባ ዘጠኝ አገሮች መሪዎች ተገኝተው ነበር፡፡

የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ንብረት ወደ መጋዘን አሽሽተዋል የተባሉ ተከሳሽ በእስራት እንዲቀጡ ተወሰነባቸው

ከአዲስ አበባ ከተማ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በአቃቂ ቃሊቲ ዕቃ ማከማቻ መጋዘን ውስጥ ከስምንት ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸውን ንብረቶች በአንድ አይሱዙ በመጫን በመጋዘን ውስጥ መደበቃቸው የተረጋገጠባቸው ተከሳሽ፣ በአንድ ዓመት ከአራት ወራት እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጠ፡፡ ቅጣት የተጣለባቸው ተከሳሽ አቶ አብዮት ከድር የሚባሉ ሲሆን፣ ያጓጓዙትን ንብረት በመጋዘናቸው ውስጥ ደብቀዋል ተብለው እንዲከላከሉ ብይን የተሰጠባቸው አቶ ጥላሁን ታደሰ ደግሞ፣ የ100 ሺሕ ብር ዋስ አስይዘው በውጭ ሆነው እንዲከራከሩ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡

ኮንትሮባንዲስቶች እነማን እንደሆኑ ለፓርላማው በግልጽ እንዲናገሩ የገቢዎችና ጉምሩክ ኃላፊዎች ተጠየቁ

የአገሪቱን ኢኮኖሚ ከመጉዳት ባለፈ የፖለቲካ ቀውስ እየፈጠሩ ናቸው የሚባሉ ‹‹ኮንትሮባንዲስቶች›› ማንነት በግልጽ ለፓርላማው እንዲቀርብ፣ የፓርላማው አባላት ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡ የፓርላማው አባላት በከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ሳይቀሩ በአገሪቱ ለሚታየው የፖለቲካ ቀውስ ጣታቸውን የሚቀስሩት ‹‹ኮንትሮባንዲስት›› በተባሉ ማንነታቸው በማይታወቅ ኃይሎች ላይ ስለሆነ፣ የእነዚህን ማንነት ፓርላማው በግልጽ የማወቅ ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ ማንነታቸው እንዲገለጽላቸው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን አመራሮችን ጠይቀዋል፡፡

ግብፃዊያን በህዳሴ ግድቡ ግንባታ ላይ የጋራ አቋም ለመያዝ ውይይት ሊያደርጉ ነው

ግብፃዊያን ኢትዮጵያ እየገነባች ባለው የህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የተለያየ አመለካከት እንዳላቸው፣ ይህንን አመለካከት ወደ አንድ ሐሳብ ለማምጣትና የጋራ አቋም ለመያዝ ውይይት ሊያደርጉ መሆኑ ታወቀ፡፡ 30ኛውን የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመካፈል የመጡና ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ ከፍተኛ የግብፅ ዲፕሎማት ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ እየገነባች ባለው የህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ አብዛኛው የግብፅ ሕዝብ ጥያቄ ያነሳል፡፡ የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስና ሁሉም ግብፃውያን የጋራ አቋም እንደሚኖራቸው ለማድረግ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ የአገሪቱ ሕዝብ ከመንግሥት አመራሮች ጋር ውይይት እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

የአፍሪካ የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ተቃውሞ ገጠመው

የአፍሪካን የአየር ትራንስፖርት አውታር ወደፊት እንደሚያራምድ የታመነበት የአፍሪካ የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ምሥረታ ተቃውሞ ገጠመው፡፡ የአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ገበያ በክልከላ የተተበተበ በመሆኑ የአፍሪካ የአየር መንገዶች ዕድገት ፈታኝ እንዳደረገው ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት የገበያ ክልከላን በማስቀረት የአፍሪካ አየር መንገዶች አፍሪካ ውስጥ በነፃነት ከአገር አገር እንዲበሩ የሚያስችል የአፍሪካ የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ምሥረታ፣ ጥር 20 እና 21 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በተካሄደው 30ኛው የኅብረቱ የመሪዎች ጉባዔ በይፋ አውጇል፡፡ ሰኞ ጥር 21 ቀን በተካሄደው የመሪዎች ጉባዔ የአፍሪካ የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ መመሥረቱን ያወጁት አዲሱ የኅብረቱ ሊቀመንበር የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ናቸው፡፡ ፖል ካጋሜ የአፍሪካ የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ምሥረታ ለአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ዕድገት ትልቅ ዕርምጃ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የሰሜን ወሎ ከተሞች ግጭት አልረገበም

በጥምቀት በዓል ማግሥት የቃና ዘገሊላን በዓል አስታኮ በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን በወልዲያ ከተማ የተከሰተው ግጭት ወደ ሌሎች የዞኑ አካባቢዎች እየተዛመተ ከመሆኑም በላይ፣ በአብዛኛው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሥራ አለመጀመራቸው ታውቋል፡፡ በወልዲያ ከተማ ሰኞ ጥር 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሦስት ቀናት የሚቆይ የሥራ አድማ መጠራቱን ሪፖርተር በሥፍራው ተገኝቶ አረጋግጧል፡፡ ከፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት የስድስት ዜጎች፣ እንዲሁም የአንድ የፀጥታ ኃይል ባልደረባ ሕይወት ከጠፋ በኋላ፣ ችግሩ ወደ ሕዝባዊ አመፅና ግርግር መቀየሩን  በዞኑ በመገኘት ለመታዘብ ተችሏል፡፡