Skip to main content
x

የደኢሕዴን ጽሕፈት ቤት ወደ ደቡብ ከተዛወረ አፈ ጉባዔዋ ከኃላፊነታቸው እንደሚለቁ ተጠቆመ

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ጽሕፈት ቤት ወደ ክልሉ ከተዛወረ፣ ሰኞ ሰኔ 18 ቀን 2010 ዓ.ም. የንቅናቄው ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ከኃላፊነታቸው ተነስተው ወደ ደቡብ ክልል እንደሚሄዱ ተጠቆመ፡፡

በቦምብ ፍንዳታው ምክንያት ኃላፊነታቸውን አልተወጡም የተባሉ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በተሾሙ 80 ቀናት ውስጥ ያሳዩትን የአመራር ለውጥና ያመጡትን ሰላም አስመልክቶ ቅዳሜ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ሕዝቡ በመስቀል አደባባይ ተገኝቶ ድጋፉን በመግለጽ ላይ እያለ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ፣ ከ150 በላይ ሰዎች በመጎዳታቸው ምክንያት ኃላፊነታቸውን አልተወጡም ተብለው የተጠረጠሩ የፖሊስ ባልደረቦችና ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

ፓርላማው ባቀረበው ወቀሳ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የተመደቡ ጥንድ ባለትዳሮችን የማቀያየር ሥራ ተጀመረ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከዲፕሎማቶች አመዳደብ ጋር በተያያዘ ከአንድ ወር በፊት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ላይ የሰላ ትችት ከቀረበ በኋላ፣ ሚኒስትሩ ወርቅነህ ገበየው (ዶ/ር) የማስተካከያ ዕርምጃ መውሰድ መጀመራቸውና እስካሁንም በሁለት ኤምባሴዎች የተመደቡ ጥንዶችን መቀየራቸው ታወቀ።

የሕዝብና የመንግሥት ሀብት በመመዝበር በሚጠረጠሩ ላይ ምርመራ መጠናቀቁ ተጠቆመ

በተደራጀና በቅንጅት የሕዝብና የመንግሥት ሀብት መዝብረዋል ተብለው በተጠረጠሩ ላይ፣ ሕጋዊ ዕርምጃ ለመውሰድ ምርመራ መጠናቀቁን የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡ የፌዴራል ፖሊስና የምርመራ ቢሮና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት በተለዩ ዘርፎች ላይ ሰፊ ምርመራ ሲያካሄዱ እንደነበር፣ ምርመራውም በአሁኑ ወቅት በመገባደድ ላይ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑት ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኤርትራ ልዑክ አቀባበል አደረጉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኡስማን ሳሌህና በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የፖለቲካ አማካሪ የማነ ገብረ አብ የተመራ የልዑካን ቡድን በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተቀብለዋቸዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ኢትዮጵያ ለውይይት የመጣውን የኤርትራ መንግሥት የልዑካን ቡድን አባላት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

በቦምብ ጥቃቱ የተጠረጠሩ 26 ታሳሪዎች ላይ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደ

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳን ጨምሮ በ26 ተጠርጣሪዎች ላይ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ቅዳሜ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድን (ዶ/ር) ለመደገፍ በተደረገ ሰልፍ ላይ ከፈነዳው ቦምብ ጋር በተገናኘ ነበር፡፡

ከተጠርጣሪዎቹ መካከል አምስቱ ኮማንደሮች፣ አንድ ምክትል ኮማንደር፣ አንድ ምክትል ኢንስፔክተር፣ ሁለት ሳጅኖች ሲሆኑ፣ 16ቱ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ናቸው፡፡

አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከፓርቲ ሊቀመንበርነታቸው ለቀቁ

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባደረገው ስብሰባ፣ የድርጅቱ ሊቀመንበር በመሆን ከየካቲት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ፡፡

አቶ ሽፈራው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትርና የደኢሕዴን ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ተክተው ነበር ወደ ሊቀመንበርነት የመጡት፡፡

አቶ ሽፈራው በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በተዋቀረው አዲሱ ካቢኔ የግብርናና የእንስሳት ሀብት ልማት ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡

ኦአነግ የትጥቅ ትግል ትቶ ወደ አገር ውስጥ ገባ

በብርጋዴር ጄኔራል ከማል ገልቹ ሲመራ የነበረው የኦሮሞ አንድነትና ነጻነት ግንባር (ኦአነግ) የትጥቅ ትግል ትቶ ወደ አገር ውስጥ ገባ፡፡

ዘጠኝ አባላት ያሉት አዲስ አበባ የገባው የልዑካን ቡድን በአቶ ተማም ባቲ የተመራ ሲሆን፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድን (ዶ/ር) ጥሪ ተቀብለው እንደመጡና ፓርቲ አቋቁመው ለመንቀሳቀስ እንደሚያስቡ ተናግረዋል፡፡ የልዑካን ቡድኑ አባላት በአሜሪካ፣ በአውሮፓና በካናዳ ሲንቀሳቀሱ ነበሩ፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ የልዑካን ቡድኑ አባላትን በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተቀብለዋቸዋል፡፡