Skip to main content
x

የቀድሞ ፍትሕ ሚኒስትርና ሚኒስትር ዴኤታ ለእነ አቶ መላኩ ፈንታ የመከላከያ ምስክርነት ሰጡ

በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል በመዝገብ ቁጥር 141352 ላይ መከላከያ ምስክሮቻቸውን በማሰማት ላይ የሚገኙት፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተርና ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣ የቀድሞ ፍትሕ ሚኒስትርና ሚኒስትር ዴኤታን በመከላከያ ምስክርነት አሰሙ፡፡

ከሃያ በላይ ኤርትራዊያን የተሳተፉበት የሕዝብ ለሕዝብ ውይይት ተደረገ

በኢትዮጵያና በኤርትራ የሕዝብ ለሕዝብ ውይይት ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የሚወክሉ ከሃያ በላይ ኤርትራውያን አዲስ አበባ መጥተው ውይይት ተካሄደ፡፡ ሴሌብሪቲ ኢቨንትስ የተሰኘ አገር በቀል ተቋም ያዘጋጀው የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት መድረክ ባለፈው ሳምንት በሐርመኒ ሆቴል ተካሂዶ ነበር፡፡ ከአሁኖቹ በተጨማሪ ወደ ፊት ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብለው ከሚታሰቡ ኤርትራዊያን ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ሰፋፊ ስብሰባዎችና ውይይቶች እንደሚደረጉ ተጠቁሟል፡፡ በእነዚህ ግለሰቦች አማካይነትና በሴሌብሪቲ ኢቨንትስ አስተባባሪነት በኤርትራ ተመሳሳይ ውይይት ለማካሄድ መታቀዱም ተገልጿል፡፡

የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ዳኛዋ ከሥራቸው እንዲሰናበቱ ያስተላለፈው ውሳኔ ጥያቄ አስነሳ

በፍርድ ቤት ተከራካሪ ወገን የዲሲፕሊን አቤቱታ ቀርቦባቸው በፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የቀረበው አቤቱታ ሲመረመር የቀረበው የዲሲፕሊን አቤቱታ ተገቢ መሆኑ በአብላጫ ድምፅ በመረጋገጡ፣ ከዳኝነት ሥራቸው እንዲሰናበቱ ውሳኔ የተላለፈባቸው የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአራዳ ሦስተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ዳኛ ጉዳይ ጥያቄ አስነሳ፡፡ ምንም እንኳን የዳኛዋ ከሥራ መሰናበት የሚረጋገጠው ወይም የመጨረሻ ውሳኔ የሚያገኘው ሹመቱን በሰጣቸው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቢሆንም፣ የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አብላጫ ድምፅ ያስተላለፈው ውሳኔ ሕግን ያልተከተለ፣ የዳኝነት ነፃነትን የሚጋፋና ተዓማኒነት የጎደለው መሆኑን ውሳኔ የተላለፈባቸው ዳኛ ይናገራሉ፡፡

አርሶ አደሮች ምርት ሰብስበው እንደ ጨረሱ ወደ መስኖ እንዲገቡ ተጠየቀ

በተያዘው የምርት ዘመን አርሶ አደሩ ያመረተውን ምርት ሰብስቦ እንደ ጨረሰ፣ የተለያዩ የውኃ አማራጮችን ተጠቅሞ ወደ መስኖ ልማት እንዲገባ ማሳሰቢያ ተሰጠ፡፡ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ መንግሥቴ ሐሙስ ታኅሳስ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፣ ከዚህ በፊት አርሶ አደሩ በዓመት አንድ ጊዜ አምርቶ ረዥም የበጋ ወራትን ያለሥራ ይቀመጥ ነበር፡፡ አርሶ አደሩ ይህንን ልምድ እንዲለውጥና ወደ መስኖ እንዲገባ ጥሪ ተላልፏል፡፡

ካቶሊክ መንግሥት አገራዊ ቁስሎችን የማዳንና ዕርቅ የማውረድ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠየቀች

በተለያዩ አካባቢዎች እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች የኢትዮጵያን ህልውናና የሕዝቡን አንድነት ከፍተኛ አደጋ ላይ የሚጥሉ ስለሆነ፣ መንግሥት አገራዊ ቁስሎችን የማዳንና ዕርቅን የማውረድ ኃላፊነት ያለበት መሆኑን የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አሳሰበች፡፡ ወቅታዊው የኢትዮጵያ ሁኔታ ያሳሰባት ቤተ ክርስቲያኒቱ በካቶሊካውያን ጳጳሳት 34ኛ መደበኛ ጉባዔዋ ከመከረች በኋላ፣ ሐሙስ ታኅሳስ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. በብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ አማካይነት መግለጫውን ሰጥታለች፡፡

ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ባላት ልዩ ጥቅም ላይ ሊካሄድ የነበረው ሕዝባዊ ውይይት ለሌላ ጊዜ ተላለፈ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ፍትህ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ባላት ልዩ ጥቅም ለመወሰን በተረቀቀው አዋጅ ላይ ሊያደርገው የነበረውን ሕዝባዊ ውይይት ለሌላ ጊዜ አስተላለፈ፡፡

ውይይቱ ከተጀመረ በኋላ ተቋርጦ ለሌላ ጊዜ የተላለፈው በውይይቱ የተገኙ የኦሮሞ ተወላጆችና የክልሉ አመራሮች፣ የክልሉ ሰላም ባልተረጋጋበት ሁኔታ በልዩ ጥቅም ጉዳይ ላይ ተረጋግተን መወያየት አንችልም በማለት ባነሱት ሐሳብ ምክንያት ነው፡፡

ውይይቱ ሊካሄድ የነበረው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዳራሽ ነበር፡፡

ከኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባለፈው ዓመት በድርጅቱ የተጀመረውን በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ አፈጻጸም በዝርዝር መገምገም ጀምሯል፡፡ በኢሕአዴግ የቆየ ባሕል መሠረት አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ፕሮግራሙን ተግባራዊ ለማድረግ በሚያካሂደው የትግል ሒደት የሚያጋጥሙትን ጉድለቶች ሰፊ ጊዜ ሰጥቶ በጥልቀት ይገመግማል። ግምገማውን መሠረት በማድረግም ራሱን በራሱ ያርማል። እነሆም የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ቀደም ሲል የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የነበሩና የተተኩ ነባር ታጋዮችን ባካተተ አግባብ ከታህሳስ 3 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ግምገማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች ግጭት የንፁኃንን ሕይወት እየቀጠፈ ነው

አህመድ ከድር (ሙሉ ስሙ ተቀይሯል) ተወልዶ ያደገው በኦሮሚያ ክልል ልዩ ስሙ አወዳይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እንደሆነ ይናገራል፡፡ አወዳይ ተወልዶ ያደገበት ከመሆኑም በላይ፣ ትዳር ይዞና ቤተሰብ መሥርቶ የሚኖርበት ከተማ እንደነበር ያስረዳል፡፡ አሁን የአምስትና የስምንት ዓመት ዕድሜ ያላቸው ልጆቹን ይዞ በአዲስ አበባ ጊዜያዊ መጠለያ ካምፕ ውስጥ እየኖረ ነው፡፡ ምክንያቱን ባላወቀው ጉዳይ ያፈራው ንብረቱ ከመቃጠሉ በተጨማሪ፣ በልጆቹ ላይ ሞት ሊያስከትል የሚችል አደጋ ተጋርጦ እንደነበር ያስታውሳል፡፡

የፓርላማ አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ እየጠበቁ ነው

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አገሪቱን ሥጋት ላይ በጣላት ብሔር ተኮር ግጭትና የፖለቲካ ቀውስ ላይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ማብራሪያ እንዲሰጧቸው ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የምክር ቤቱ አባላት ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ አግኝቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ እስኪገኙ ድረስ መደበኛ ስብሰባዎችን ማካሄድ ተገቢ አይደለም የሚል አቋም ይዘዋል፡፡

ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላትን ልዩ ጥቅም ለመወሰን በተረቀቀው አዋጅ ላይ ሕዝባዊ ውይይት ተጠራ

 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕና አስተዳደር እንዲሁም የከተማና ኮንስትራክሽን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላትን ልዩ ጥቅም ለመወሰን የተረቀቀውን የሕግ ሰነድ በዝርዝር ለመመልከት ሕዝባዊ ውይይት ጠሩ።