Skip to main content
x

የኢትዮ ጂቡቲ ዋና መንገድ ቢከፈትም ሥጋቶች እንዳሉ ተጠቆመ

ከቀናት በፊት በአፋር ክልል በሚገኙ ቀበሌዎች ባገረሸው ግጭት ሳቢያ የኢትዮ ጂቡቲ ዋና መንገድን ጨምሮ፣ ከክልሉ ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚያቀኑ መንገዶች ለቀናት ተዘግተው ቢከፈቱም አሁንም ሥጋቶች እንዳሉ ታወቀ፡፡

በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ ኃላፊ የነበሩ ተጠርጣሪ በ100 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተሰጠ

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከሁለት ወራት በላይ በእስር የቆዩት የኢትዮ ቴሌኮም የኤንጂፒኦ ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ኢሳያስ ዳኛው በ100 ሺሕ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አሥረኛ ወንጀል ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ሰኞ ጥር 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ከግምት በላይ ሆቴል በመሸጥ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው መጠርጠራቸው ተገለጸ

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ 51 ሚሊዮን ብር ግምት ያለውን ኢምፔሪያል ሆቴል በ75 ሚሊዮን ብር ለሜቴክ በመሸጥ፣ 24 ሚሊዮን ብር ጉዳት አድርሰዋል ተብለው መጠርጠራቸው ተገለጸ፡፡

አቶ ኤርሚያስ ለፖሊስ የመመርመሪያ አንድ ቀን እንኳን ሊሰጠው አይገባም በማለት የተከራከሩ ሲሆን፣ ፖሊሶቹ ባይለወጡ እንኳ እናንተ አትለወጡም ወይ በማለት ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡

ካሁን ቀደም በተመሳሳይ የፖሊስ ባልደረባ ለ128 ቀናት መታሰራቸውን ያስታወሱት አቶ ኤርሚያስ፣ ፖሊሶች ለምን አይቀየሩም በማለት በለቅሶ አስረድተዋል፡፡

የሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ወንድም የ100 ሺሕ ብር ዋስትና ተፈቀደላቸው

የሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው በ100 ሺሕ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ወሰነ፡፡ የቀድሞ የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰር አቶ ኢሳያስ ተጠርጥረው በእስር የቆዩት ኢትዮ ቴሌኮም በሶማሌ ክልልና በባሌ ዞን የሚያስተክለውን የሞባይል ኔትወርክ ማስፋፊያ ማማ ተከላ ያለጨረታ ለሜቴክ ሰጥተዋል በሚል ነበር፡፡

የቀድሞ የሜቴክ ኃላፊዎች ከመርከቦች ግዥ ጋር በተገናኘ የ544.7 ሚሊዮን ብር ክስ ተመሠረተባቸው

የሜቴክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ 12 ኃላፊዎችና ሁለት ግለሰቦች ከመርከቦች ግዥ ጋር በተገናኘ 544.7 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ የሙስና ወንጀል ክስ ሰኞ ጥር 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ተመሠረተባቸው፡፡

መዋሀድ የከበዳቸው የመድረክ አባል ፓርቲዎች

አወዛጋቢው ምርጫ 97 በፖለቲከኞች፣ በሲቪክ ማኅበራት አመራሮች፣ እንዲሁም በጋዜጠኞች እስር መቋጨቱን ተከትሎ የአገሪቱ የፖለቲካ ምኅዳር ጭርታና ድብታ ወሮት ነበር፡፡ ይህንን ድብታ ለመስበር በሚመስል ሁኔታ የፖለቲካ ምኅዳሩን የተቀላቀለው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ)፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ በመሆን ለመሥራት እንቅስቃሴውን በ2000 ዓ.ም. ጀመረ፡፡

ኢዜአ አገራዊ መግባባትንና የአገር ገጽታን ለመገንባት የሚሠራ ሚዲያ ሆኖ እንዲቋቋም ረቂቅ ሕግ ቀረበ

ላለፉት 75 ዓመታት የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) የአገሪቱን የልማት፣ የዴሞክራሲና የሕዝቦችን በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ ግንኙነትና አንድነት፣ እንዲሁም የአገሪቱን ገጽታ ለመገንባት የሚሠራ ሆኖ በድጋሚ እንዲቋቋም ረቂቅ ሕግ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡

‹‹ዛሬ ነገ እየተባለ የጠፋው ጊዜ ከባድ ጉዳት አድርሷል›› የአገር መከላከያ ሠራዊት ምክትል ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ

በተደረገለት የሰላም ጥሪ መሠረት አገር ቤት ገብቶ በሰላም ለመንቀሳቀስ ከኤርትራ የተመለሰው በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ‹‹ሸኔ›› የተባለው የኦነግ ቡድን፣ ከኤርትራ ይዞት ከመጣው ውጪ ሠራዊቱን ካምፕ ባለማስገባቱና ዛሬ ነገ እየተባለ በባከነው ጊዜ ምክንያት ከባድ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ፡፡

በሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጥረው የታሰሩ የደኅንነት ሠራተኞች የሚስጥር ስም ‹‹አቤ ከቤ›› እንደነበር ተገለጸ

በከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሠራተኞች የነበሩ ግለሰቦች የሚስጥር ስም፣ ‹‹አቤ ከቤ›› እንደነበር ዓቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤት ተናገረ፡፡

በምዕራብ ጎንደር በተፈጠረው ግጭት የነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ድንበር ላይ ቆመዋል

ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን በተፈጠረ ግጭት ሳቢያ፣ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ነዳጅ የሚያመላልሱ የነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች መተማ ከተማ ለመቆም እንደተገደዱ ተገለጸ፡፡