Skip to main content
x

የሕግ የበላይነትን የሚፈታተኑ ድርጊቶች ይወገዱ!

መንግሥት ሰሞኑን በመጀመርያ ዙር 528 ሰዎች ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር እንደሚለቀቁ አስታውቋል፡፡ እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው ደግሞ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለ17 ቀናት ያደረገውን ግምገማ ካጠናቀቀ በኋላ ባወጣው ባለ ስምንት ነጥብ ውሳኔ መሠረት ነው፡፡ ከፖለቲካ ጋር በተገናኘ ክሳቸው እንዲቋረጥ የተደረጉ ሰዎች ከእስር መፈታታቸው መልካም ጅምር ነው፡፡ በዚህ መሠረት ሒደቱ ቀጥሎ በርካቶች ከእስር እንደሚለቀቁ ይጠበቃል፡፡

የኢኮኖሚው ጣጣ ሌላ ቀውስ እንዳያመጣ!

ላለፉት ሁለት ዓመታት አገሪቱ ያጋጠማት የፖለቲካ ቀውስ በዜጎች ሕይወት፣ አካልና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡ በበርካቶች ላይም የሥነ ልቦና ችግር  አስከትሏል፡፡ የፖለቲካ ቀውሱ የፈጠራቸው ተጓዳኝ ችግሮች በኢኮኖሚው ላይ በስፋት እየታዩ ነው፡፡ ሁከት በተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች በተደጋጋሚ የጥቃት ሰለባ የሆኑ የአገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስትመንቶች መጠነ ሰፊ ጉዳት አጋጥሟቸዋል፡፡

የአገር ችግር የሚፈታው በኢሕአዴግ ብቻ አይደለም!

ኢትዮጵያ ለገጠማት ችግር የማያዳግም መፍትሔ ያለው ሕዝቧ ዘንድ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጠረፍ እስከ ጠረፍ በአገሩ ጉዳይ ተሳታፊ ሆኖ ሐሳቡን በነፃነት መግለጽ ሲችል፣ አሁን ላጋጠመው አገራዊ የጋራ ችግር ሁነኛ መፍትሔ ያመነጫል፡፡ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለመግለጽ እንደተሞከረው ከአገር ህልውና በላይ ምንም ነገር የለም፡፡ ግለሰብም ሆነ ቡድን ከአገር በላይ መሆን አይችሉም፡፡

አገርም ሕዝብም ተንፈስ ይበሉ!

አገርን እንደ ንፋፊት ቀስፎ የያዛትን ውጥረት የሚያረግብ ተስፋ ሲሰማ ሕዝብ  ተንፈስ ይላል፡፡ ሰሞኑን ከገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ አመራሮች የተሰማው ራስን መውቀስና ወደ ትክክለኛው ጎዳና የመመለስ ተስፋ አገርንም ሕዝብንም ተንፈስ ያደርጋል፡፡ የኢሕአዴግ አራቱ ብሔራዊ ድርጅቶች ሊቃነ መናብርት በጋራ በሰጡት መግለጫ፣ በውስጣቸው የነበረውን ፀረ ዴሞክራሲ አስተሳሰብና አሠራር በማስወገድ አገርንና ሕዝብን የሚያስቀድም ዴሞክራሲያዊ አሠራር ለማስፈን በቁርጠኝነት መነሳታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ከመግለጫው በላይ ተግባር ይጠበቃል!

መሰንበቻውን የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ ለ17 ቀናት ባካሄደው ግምገማ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች በመምከር፣ የሐሳብ አንድነትና መተማመን በመፍጠር ውሳኔዎች ማስተላለፉን አስታውቋል፡፡ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በአገሪቱ የሚታዩ የቆዩና ወቅታዊ ችግሮችን ከእነ ዝርዝር መገለጫቸው በመለየት፣ በመንስዔና በመፍትሔዎቻቸው ላይ በመነጋገር ችግሮችን ለመቅረፍ ቃል ገብቷል፡፡

ቅድሚያ ለአገር ህልውና!

 የአገር ጉዳይ ሲነሳ በቅድሚያ የሚታሰበው ህልውና ነው፡፡ ዕድሜ ጠገቡ ብሂል የሚለውም፣ ‹‹አባት ቢሞት በአገር ይለቀሳል፣ እናት ብትሞት በአገር ይለቀሳል. . . አገር የሞተ ዕለት ወዴት ይደረሳል?›› ነው፡፡ ከዚህ ጥልቀትና ስፋት ያለው አባባል መረዳት የሚቻው በአገር ህልውና መደራደር እንደማይቻል ነው፡፡ የአንድ አገር ዜጎች በተለያዩ ጉዳዮች ግላዊም ሆነ ቡድናዊ አቋሞች ሊኖሩዋቸው ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዋስትናው አንድነቱ ብቻ ነው!

‹‹አንድ ከሆንን ፀንተን እንቆማለን፣ ከተከፋፈልን ግን እንገረሰሳለን›› የሚባለው ታዋቂ አባባል በዓለም ዙሪያ ሰፊ ተቀባይነትን ያገኘ ነው፡፡ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ደግሞ አንድነት ትልቅ ትርጉም አለው፡፡ የአንድነትን ትርጉም ለመግለጽ ‹‹ድር ቢያብር አንበሳ ያስር››፣ ‹‹ለአንድ ብርቱ ሁለት መድኃኒቱ››፣ ‹‹ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሃምሳ ሰው ጌጡ››፣ ወዘተ. ዕድሜ ጠገብ አገር በቀል አባባሎች በስፋት ይታወቃሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ የሚታወቀውም የሚወዳት አገሩን ከባዕዳን ወራሪዎችና ተስፋፊዎች ለመከላከል በከፈለው ወደር የሌለው መስዋዕትነት ነው፡፡

የመላውን ሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎች መፍታት የሚቻለው በትክክለኛ ቁመና ላይ በመገኘት ብቻ ነው!

በሩን ዘግቶ ለበርካታ ቀናት ስብሰባ የተቀመጠው የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መሰንበቻውን በመሀል ባወጣው መግለጫ፣ ራሱን በመገምገም ከነባራዊው ሁኔታ ጋር የሚመጥን ድርጅታዊ ቁመና ለመያዝ ያላሰለሰ ጥረት እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ በአገሪቱ የሚስተዋሉ ችግሮችን በተመለከተ ባደረገው ግምገማም የችግሮቹ ዓይነተኛ ባህሪያትና ዋነኛ መንስዔዎች ላይ ዝርዝር ውይይት መደረጉን፣ ለችግሮቹም የማያዳግምና መሠረታዊ የሆነ መፍትሔ እንደሚሰጥ ገልጿል፡፡

አገር የጠላት መጫወቻ እንዳትሆን!

በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ የተለያዩ ሥፍራዎች እያጋጣሙ ባሉ ግጭቶች የንፁኃን ሕይወት እየጠፋ ነው፣ የነገን ተስፋ የሚያጨልሙ አሳዛኝ ድርጊቶች እየተፈጸሙ ነው፡፡ በተለይ ሰሞኑን በዜጎች ላይ የተፈጸሙ ግድያዎች ያሳምማሉ፡፡ አገርን እየገጠመ ያለው መከራ ከሐዘን መግለጫ በላይ ነው፡፡ ሲያስቡት ይቀፋል፣ ያሳፍራል፣ ቃላት ሊገልጹት ከሚችሉት በላይ መራር የሆነ ስሜት ይፈጥራል፡፡ መንግሥት ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ እያጋጠሙ ላሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ሁሉንም ወገን የሚያስማማ ጠብሰቅ ያለ መፍትሔ ማምጣት አቅቶት አገር ቋፍ ውስጥ ትገኛለች፡፡ ራሱ የፈጠራቸውን ችግሮች ማስተካከል አቅቶት በተፈጠረው ክፍተት ጠላት እየገባ ነው፡፡

አገር እስካሁን ያለችው በጨዋው ሕዝብ እንጂ በብቁ አመራር አይደለም!

ኢትዮጵያ እስካሁን ያለችው በዚህ ጨዋና ኩሩና አስተዋይ ሕዝብ ምክንያት እንጂ፣ በብቁ አመራር አለመሆኑ አሁን በትክክል ግልጽ እየሆነ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ጨዋና ኩሩ ሕዝብ በአስተዋይነቱና በአርቆ አሳቢነቱ ሳቢያ እርስ በርሱ ከመደጋገፍ በላይ፣ የሚወዳት አገሩ ክፉ እንዳይነካት ሲል በርካታ ችግሮችን ችሎ ኖሯል፣ እየኖረም ነው፡፡ ከአስመራሪው ድህነትና እንደ እሳት ከሚጋረፈው የኑሮ ውድነት ጋር እየታገለ፣ በየደረጃው ያሉ የአገር አስተዳዳሪዎችን በትዕግሥት ብዙ ጠብቋቸዋል፡፡ በስሙ ከሚነግዱበት ጀምሮ በአጉል ተስፋ እስከሚቀልዱበት ድረስ ከሚፈለገው በላይ ታግሷቸዋል፡፡