Skip to main content
x

ትኩረት ለዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች!

ከ100 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት የአሁኗ ኢትዮጵያ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ መስኮች ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ወደፊት መገስገስ አለባት፡፡ ይህ ግስጋሴ እንዲቀላጠፍ ደግሞ የአገር ጉዳይ ያገባናል የሚሉ በሙሉ ዕገዛ የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው፡፡

የሚያዋጣው ከአጥፊና ጠፊ ፖለቲካ መላቀቅ ነው!

የኢትዮጵያ የፖለቲካ አጉል ልማድ ጠላት ማፍራት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ የገዛ ወገንን በፖለቲካ አቋም ልዩነት ምክንያት በመፈረጅ፣ የአጥፊና ጠፊ ትርክት ውስጥ መዘፈቅ የዓመታት ሕመም ነው፡፡ ከዚህ ዓይነቱ አሳዛኝና ኋላቀር ዕሳቤ ውስጥ በመውጣት ልዩነትን መቀበል መለመድ አለበት፡፡

ኢትዮጵያ ላይ አትዶልቱ!

ኢትዮጵያ ከሥልጣን በላይ ናት፡፡ ኢትዮጵያ ከማናቸውም ጥቅማ ጥቅሞች በላይ ናት፡፡ ኢትዮጵያን የማያስቀድም ሥልጣን፣ ጥቅም ወይም ሌላ ነገር ተቀባይነት የለውም፡፡ ኢትዮጵያን ከራሳችሁ ሥልጣንና ጥቅማ ጥቅም በታች የምትመለከቱ ፖለቲከኞች፣ አክቲቪስቶች ወይም ሌላ መጠሪያ ያላችሁ ሁሉ እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ፡፡

የሩዋንዳ አስከፊ ታሪክ በኢትዮጵያ እንዳይደገም!

እሑድ መጋቢት 29 ቀን 2011 ዓ.ም. የሩዋንዳ የጅምላ ጭፍጨፋ 25ኛ ዓመት መታሰቢያ ሲዘከር፣ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ይህ አሳዛኝ ታሪክ በኢትዮጵያ ምድር እንዳይደገም ድምፃቸውን አሰምተዋል፡፡ የዛሬ 25 ዓመት 800 ሺሕ ቱትሲዎችና ለዘብተኛ ሁቱዎች በጥላቻ ባበዱ ሰዎች ቅስቀሳ ያለ ምሕረት በሩዋንዳ ምድር ተጨፍጭፈዋል፡፡

ለሰላም ቅድሚያ ያልሰጠ የትኛውም ዓላማ በአጭር ይቀጫል!

ኢትዮጵያ ከፊቷ በርካታ ሥራዎች ተደቅነዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ተቀዳሚ ተግባር በመላ አገሪቱ አስተማማኝ ሰላም ማስፈን መሆን አለበት፡፡ ሰላም በሌለበት የፖለቲካ ምኅዳሩን በሚፈለገው መጠን ለመክፈት ያዳግታል፡፡

አለመደማመጥ አገርን ለኪሳራ ይዳርጋል!

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የአንድ ዓመት የሥልጣን ቆይታ፣ በታሪክ ሊታወሱ የሚችሉ በርካታ አገራዊ ጉዳዮች ተከናውነውበታል፡፡ ከእነዚህ ጉዳዮች መካከል ብዙዎቹ አገርን ከአንድ ምዕራፍ ወደ ሌላ የሚያሸጋግሩና በአዎንታዊነት ተጠቃሽ ሲሆኑ፣ አገርን ለአደጋ የሚዳርጉ አስፈሪ ክስተቶችም ተስተውለዋል፡፡

አዲስ አበባ የጽንፈኝነት ሒሳብ ማወራረጃ መሆን የለባትም!

የአዲስ አበባ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ጥያቄ የማንሳትም ሆነ የመፍትሔ ሐሳብ የማቅረብ መብት አለው፡፡ በአዲስ አበባ ጉዳይ የሚደረግ ንግግርም ሆነ ውይይት፣ ክርክርም ሆነ ድርድር ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መሆን ይኖርበታል፡፡

የፖለቲካው ስብራቶች የሚጠገኑት በሐሳብ ነፃነት ብቻ ነው!

ኢትዮጵያ ውስጥ የሐሳብ ነፃነት ሳይከበር ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ይገነባል ብሎ መጠበቅ፣ ከእባብ እንቁላል እርግብ ይፈለፈላል ብሎ ተስፋ የማድረግ ያህል ነው፡፡ የሐሳብ ነፃነት መከበር ያለበት በመንግሥት ብቻ ሳይሆን በፖለቲከኞች፣ በሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች፣ በምሁራን፣ በወጣቶች፣ በሴቶችና በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ነው፡፡

የማይጨርሱትን አይጀምሩትም!

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አስተዳደር በይፋ ሥራ ከጀመረ አንድ ዓመት ሊሆነው ቀናት ብቻ ይቀሩታል፡፡ በአንድ ዓመት ውስጥ የተከናወኑ ሥራዎችና ያጋጠሙ ችግሮች በግልጽ ይታወቃሉ፡፡ ኢትዮጵያ ለዘመናት ሲንከባለሉ ከመጡ ችግሮች ተላቃ ወደ ታላቅ አገርነት ሊያሸጋግሯት የሚችሉ ተስፋ ሰጪ ጅምሮች የታዩትን ያህል፣ ዓይታው ወደማታውቀው አደገኛ ቁልቁለት የሚያንደረድሯት ክስተቶችም አጋጥመዋታል፡፡