Skip to main content
x

ከታሪክ አለመማር የአገር ራዕይ ያጨናግፋል!

የዘመነ መሳፍንት ሥርዓትን በመናድ የማዕከላዊ መንግሥት ምሥረታን የጠነሰሱትና ለዘመናዊ ኢትዮጵያ ግንባታ መሠረት የጣሉት አፄ ቴዎድሮስ 200ኛ ዓመት የልደት በዓል በሚዘከርበት ሰሞን፣ አንዳንድ መሠረታዊ ጉዳዮችን እያወሱ የጊዜው ሁኔታ ላይ መነጋገር የግድ ይላል፡፡

ኃላፊነት በጎደላቸው ድርጊቶች ምክንያት አገር አይታመስ!

ሕዝብና አገርን ችግር ውስጥ የሚከቱ ኃላፊነት የጎደላቸው ድርጊቶች እየተበራከቱ ነው፡፡ እነዚህ ድርጊቶች በአመዛኙ እየተፈጠሩ ያሉት ለሕዝብም ሆነ ለአገር ኃላፊነት በማይሰማቸው ወገኖች ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በይፋ መንበረ ሥልጣኑን ከተቆጣጠሩ ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም

የአገር ጉዳይ የልጆች ጨዋታ አይደለም!

በዚህ ዘመን ምራቃቸውን የዋጡ ሰዎች የወጣቶች መካሪ፣ የአገር ሽማግሌ፣ የትውልድ አርዓያና የተጣመመውን የሚያቀና መሆን ሲገባቸው፣ እንደ ሠፈር ጎረምሳ የብጥብጥና የሁከት ምንጭ ሲሆኑ ያሳዝናል፡፡ በፖለቲካው መስክ ከ40 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠሩ ፖለቲከኞችና የሚመሩዋቸው ድርጅቶች አድረው ቃሪያ ሲሆኑ ያሳፍራል፡፡ ለዓመታት በመሣሪያ ያልተሳካላቸውንና በሰላማዊ ጥሪ ያገኙትን መልካም አጋጣሚ የሚያበላሹ ያሳቅቃሉ፡፡

የአገር ተስፋ በእኩያን አይጨናገፍ!

የኢትዮጵያ ሕዝብ በአራቱም ማዕዘናት ከዳር እስከ ዳር ለሰላም፣ ለዴሞክራሲና ለብልፅግና የሚደረገውን ጉዞ ለማገዝ በአንድነት መነሳቱን በተደጋጋሚ አስታውቋል፡፡ ይህንን ጉዞ ለማጨናገፍ የሚርመሰመሱ እኩያን ደግሞ ከተለያዩ አቅጣጫዎች እያደቡ ጥቃት ፈጽመውበታል፡፡

ሰላም ከቃል በላይ ተግባር ይሻል!

ቃልና ተግባር አልገናኝ እያለ እንጂ ስለሰላም ያልተባለ ነገር የለም፡፡ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን፣ ፖለቲከኞችና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በተገኘው አጋጣሚ ስለሰላም ብዙ ብለዋል፡፡

አገር በፕሮፓጋንዳ አትፈርስም!

የአገር ጉዳይ ሲባል የተወሰኑ ቡድኖች ወይም ስብስቦች ሳይሆን፣ የመላው ሕዝብ ጉዳይ ማለት ነው፡፡ ማንም በተደሰተና በከፋው ጊዜ እየተነሳ አገርን መገንባት ወይም ማፍረስ አይችልም፡፡ አገር የመላው ሕዝብ አንጡራ ሀብት ናት የሚባለው፣ የሁሉም ነገር ሉዓላዊ ባለቤት ሕዝብ በመሆኑ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግሞ በታሪኩ የሚታወቀው፣ አገሩን ከማናቸውም ዓይነት ጥቃቶች ሲጠብቅና ደሙን አፍስሶ የሕይወት መስዋዕትነት ሲከፍልላት ነው፡፡

ከስህተቱ የማይማር የትውልድ መሳቂያ ይሆናል!

‹‹ብልህ ከሌሎች ስህተት ሲማር ሞኝ ግን ከራሱም አይማርም›› የሚለው ዕድሜ ጠገብ አባባል ትልቅ መልዕክት አለው፡፡ የሰው ልጅ በሥራ ላይ ሲሆን ስህተት ሊያጋጥመው ይችላል፡፡ ‹‹ከሰው ስህተት ከብረት ዝገት አይጠፋም›› የሚል የዛገ ተረት እየተረተ መኖር ግን አይችልም፡፡

ከሴራ ፖለቲካ ማንም አያተርፍም!

የኢትዮጵያን የፖለቲካ ምኅዳር ካበላሹት በርካታ ከንቱ ነገሮች መካከል አንዱ ሴረኝነት ነው፡፡ ሴረኝነት የኢትዮጵያን መልካም አጋጣሚዎች ከማበላሸት አልፎ የበርካቶችን ሕይወት የቀጠፈ፣ ያሰቃየ፣ ለስደት የዳረገና ተስፋ ያስቆረጠ ነው፡፡

ሕዝብ በአገሩ ህልውና አይደራደርም!

በአገሪቱ የተለያዩ አቅጣጫዎች የሚደመጡ ነገሮች ከተስፋ ይልቅ ለሥጋት እያደሉ ነው፡፡ ከመጠን በላይ ራስ ወዳድነት የተጠናወተውና አርቆ አሳቢነት የጎደለው የተወሰኑ ወገኖች ድርጊት ሕዝብን ሰላም እየነሳ ነው፡፡

ፍትሕ የሕዝብና የአገር ጋሻ ይሁን!

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት ተጠምቶ የኖረው ፍትሕ ነው፡፡ ፍትሕ በመጥፋቱ ምክንያት ኢትዮጵያውያን ለዘመናት የጭቆና ቀንበር ሲሸከሙ ኖረዋል፡፡ ሕይወታቸውን ገብረዋል፡፡ አካላቸው ጎድሏል፡፡ ንብረታቸው ተዘርፏል፡፡