Skip to main content
x

ታላቅ መሆን የሚቻለው ያለፈውን በማንኳሰስ መጪውን በማጨለም አይደለም!

ከአፍሪካ አንድነት መሥራች አባቶች መካከል ግንባር ቀደም የሆኑት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በወታደራዊው መንግሥት ከሥልጣን ከተወገዱ ከ44 ዓመታት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ፣ ሰሞኑን በተካሄደው በ32ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ሐውልታቸው በከፍተኛ ሥነ ሥርዓት ይፋ ተደርጓል፡፡

የጋራ እሴቶችን የሚንዱ ነውረኞች በሕግ አደብ ይግዙ!

‹‹ካልደፈረሰ አይጠራም›› በሚል አጉል ብሒል የተለያዩ ግጭቶች እየተቀሰቀሱ፣ በሕዝብ ሕይወትና ንብረት ላይ የሚዘገንኑ ድርጊቶች ተፈጽመዋል፡፡ ብሔርን ወይም ማንነትን ተገን ያደረጉ እርኩሳዊ ድርጊቶችን ወደ ሃይማኖት መውሰድ በጣም አደገኛ ነው፡፡

የሥልጡን ፖለቲካ የጨዋታ ሕግ እፍርታም አይፈልግም!

ኢትዮጵያ ትልቅ አገር ናት ሲባል ለስታትስቲክስ ቀመር ማሟያ ብቻ አይደለም፡፡ ነገር ግን ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ በተዘረጋው ሰፊ ምድሯ ውስጥ የተለያዩ ማንነቶችን፣ ቋንቋዎችን፣ ባህሎችን፣ እምነቶችንና የአኗኗር ዘይቤዎችን ይዘው ኅብረ ብሔራዊነትን ጌጥ አድርገው የሚኖሩ 108 ሚሊዮን ያህል ዜጎች አገር ናት፡፡

ከፖለቲካው ባልተናነሰ የኢኮኖሚው ጉዳይ ያሳስባል!

በአሁኑ ጊዜ ከአነስተኛ የንግድ ሥራዎች እስከ ትልልቅ ኢንቨስትመንቶች ድረስ ከፍተኛ የሆነ መቀዛቀዝ ይታይባቸዋል፡፡ አገር ጤና ሆኖ ውሎ ማደር ሲያቅተው እንኳን የተትረፈረፈ ምርት ይዞ ገበያ መውጣትም ሆነ መሸመት፣ በሰላም ወጥቶ መግባትም ያዳግታል፡፡ ለአገር ውስጥ ፍጆታ የሚውሉና የኤክስፖርት ምርቶች  እንደ ልብ ገበያ ውስጥ ሳይቀርቡ፣ ከውጭ የሚገቡ መሠረታዊ አቅርቦቶችም እክል ሲገጥማቸው ሠርቶ አዳሪውንም ሆነ ሥራ ፈላጊውን ያስደነግጣል፡፡

ተስፋ ባላት አገር በሥጋት ተከቦ መኖር ይብቃ!

የአገር ጉዳይ ሲነሳ በተስፋ የተሞሉ መልካም አጋጣሚዎች እንዳሉ ሁሉ፣ በሥጋት የተሞሉ ክፉ ነገሮችም አሉ፡፡ የአገራቸው ዕጣ ፈንታ ከሚያሳስባቸው ቅን ዜጎች ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ አንቱ የተባሉ ስመጥር ሰዎች ድረስ፣ ተስፋና ሥጋት በተለያዩ ፈርጆች ይተነተናሉ፡፡

ጥራዝ ነጠቅነት የአገር ጠንቅ እየሆነ ነው!

የ19ኛው ክፍለ ዘመን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሊቅ ጀርመናዊው ካርል ማርክስ ከተናገራቸው መሠረታዊ ነጥቦች መካከል አንዱ፣ ‹‹ፈላስፎች ዓለምን በተለያዩ መንገዶች ተርጉመዋል፣ ዋናው ቁም ነገር ግን ዓለምን መለወጥ ነው፤›› የሚለው ይገኝበታል፡፡

ከታሪክ አለመማር የአገር ራዕይ ያጨናግፋል!

የዘመነ መሳፍንት ሥርዓትን በመናድ የማዕከላዊ መንግሥት ምሥረታን የጠነሰሱትና ለዘመናዊ ኢትዮጵያ ግንባታ መሠረት የጣሉት አፄ ቴዎድሮስ 200ኛ ዓመት የልደት በዓል በሚዘከርበት ሰሞን፣ አንዳንድ መሠረታዊ ጉዳዮችን እያወሱ የጊዜው ሁኔታ ላይ መነጋገር የግድ ይላል፡፡

ኃላፊነት በጎደላቸው ድርጊቶች ምክንያት አገር አይታመስ!

ሕዝብና አገርን ችግር ውስጥ የሚከቱ ኃላፊነት የጎደላቸው ድርጊቶች እየተበራከቱ ነው፡፡ እነዚህ ድርጊቶች በአመዛኙ እየተፈጠሩ ያሉት ለሕዝብም ሆነ ለአገር ኃላፊነት በማይሰማቸው ወገኖች ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በይፋ መንበረ ሥልጣኑን ከተቆጣጠሩ ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም