Skip to main content
x

የሚያዋጣው በሥርዓት መምራትና መመራት ነው!

ተወደደም ተጠላም ለአገር የሕግ የበላይነት ያስፈልጋል፡፡ በሕግ የበላይነት የማይተዳደር አገር የሥርዓት አልበኞች መፈንጫ ይሆናል፡፡ የሕግ የበላይነት ማለት ደግሞ ሁሉም ዜጎች በሕግ ፊት እኩል የሚሆኑበትና የሚዳኙበት ነው፡፡ በሕግ የበላይነት ስም ግን አድልኦና ሸፍጥ የሚፈጸም ከሆነ፣ የምንነጋገረው ስለሕገወጥነት ይሆናል ማለት ነው፡፡

የሕዝብን ቀልብ የሚገዛው የላቀ ሐሳብ ብቻ ነው!

መልካም አጋጣሚዎችን በማምከን የሚታወቀው የኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ በመስዋዕትነት የተገኘውን ለውጥ ለመቀልበስ ለሚያግዝ ከንቱ ትንቅንቅ መደላድል እየፈጠረ ነው፡፡ ሕዝብ የዴሞክራሲ ጭላንጭል እያየ ተስፋ ሰንቆ አዲሱን ዓመት በተቀበለ ማግሥት፣ የተጀመረውን ለውጥ መቀመቅ የሚከት ሰቅጣጭ ጥቃት በወገኖቻችን ላይ ተፈጽሟል፡፡

ነውጠኛ ባህሪያት ለአገር አይጠቅሙም!

ኢትዮጵያን ከአምባገነናዊ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማሸጋገር የሚቻለው፣ ነውጠኛ ባህሪያትን አስወግዶ ዴሞክራሲያዊነትን በመላበስ ነው፡፡ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚገነባው ደግሞ ልዩነቶችን ማክበርና መቀበል ሲቻል ነው፡፡ ዴሞክራሲ አፋኝነትን፣ ጉልበተኝነትንና ጥጋበኝነትን ማስተናገድ አይችልም፡፡

አዲሱን ዓመት በአዲስ መንፈስ እንቀበለው!

አሮጌው ዓመት ተሸኝቶ አዲሱ ሲገባ መንፈስን ማነቃቃትና መልካም ነገሮችን መመኘት የተለመደ ነው፡፡ ሁሌም በአዲስ ዓመት መቀበያ ላይ መልካም ምኞቶችን መለዋወጥ፣ ሥጦታ መሰጣጠት፣ መደጋገፍና ብሩህ ተስፋ መሰነቅ በኢትዮጵያውያን ዘንድ የተለመደ ነው፡፡

ትኩረት ለትልልቅ አገራዊ ጉዳዮች!

የአገር ጉዳይ ሲባል የመላው ሕዝባችን ጉዳይ ማለት ነው፡፡ የአገራችን ሕዝብ ከምንም ነገር በላይ የሚያሳስበው የአገሩ ህልውና ነው፡፡ ይህ ህልውና ዘላቂና አስተማማኝ የሚሆነው ደግሞ ኢትዮጵያዊያን የጋራችን ናቸው የሚሏቸው ጥቅሞችና ፍላጎቶች በእኩልነት ሲከበሩ ነው፡፡

የኢትዮጵያዊነት የጋራ እሴቶች ይከበሩ!

ኢትዮጵያዊነት በጀግኖች ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ከትውልድ ወደ ትውልድ የተሸጋገረ የኅብረ ብሔራዊነት መገለጫ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር በጥቅብ ያቆራኙት የጋራ እሴቶቹ የሚደምቁት በኢትዮጵያዊነት ነው፡፡

ልጓም ያልተበጀለት ሥልጣን የሴረኞች መጫወቻ ይሆናል!

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለአኗኗር ዘይቤዎቹ የሚጠቀምባቸው በርካታ ምሳሌዎችና አባባሎች አሉት፡፡ ቋንቋና ባህል ሳይገድባቸው የሚመሳሰሉ አባባሎች በርካታ ናቸው፡፡ ሕዝብ ብርቱውን የበለጠ ለማበረታታት፣ ደከም ያለውን ለማነቃቃት፣ ጥሩ የሠራውን ለማሞገስና ያጠፋውን ለመገሰፅ የሚጠቀምባቸው ምሳሌዎች አስተማሪነት አላቸው፡፡

የኢትዮጵያ መፃኢ ዕድል የሚወሰነው በልጆቿ ብቻ ነው!

የኢትዮጵያ መፃኢ ዕድል የሚወሰነው በልጆቿ ብቻ እንደሆነ የሚፈተንበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ ኢትዮጵያ ልጆቿ በተለያዩ የአስተሳሰብ ምህዋሮች ውስጥ ቢገኙም፣ በአገር የጋራ ጉዳይ ላይ ግን በጣም የተቀራረበ አቋም ሊያንፀባርቁ ይገባል፡፡