Skip to main content
x

ነፃ የቢዝነስ ውድድር ለጤናማ ኢኮኖሚ

በነፃ ገበያ ሥርዓት ውስጥ ውድድር የግድ ነው፡፡ ውድድሩ ግን ጤናማ መሆን ይኖርበታል፡፡ አገራችን ነፃ ገበያና ነፃ ሥርዓት እየተከተለች ነው ቢባልም፣ በአግባቡ እየተተገበረ ነው ማለት አይቻልም፡፡ መንግሥት እንደ አንድ ተወዳዳሪ ከግሉ ዘርፍ ጋር ፉክክር በሚገባበት አገር እንዴት ነፃ ገበያ ይታሰባል ሊባል ይችላል፡፡

መልካም ስም ከሽቶ በላይ ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰባ ዓመታት በላይ በዘለቀው የአገልግሎት ታሪኩ አስከፊ ከሆኑ አደጋዎች አንዱን ከሰሞኑ አስተናግዷል፡፡ ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ 157 መንገደኞችንና የበረራ ሠራተኞችን በማሳፈር ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ መጓዝ በጀመረ በስድስት ደቂቃ ውስጥ ካሰበበት ሳይደርስ ከተከሰከሰ ሳምንት አስቆጥሯል፡፡

ሰላም እናውርድ

ሰላም ለሁሉም ፍላጎታችን መሳካት መሠረት ነው፡፡ ያለ ሰላም ዕቅዶቻችንንም አገራዊ ራዕያችንንም ከግብ ለማድረስ አንችልም፡፡ ሰላም ማጣት የሚያስከፍለው ዋጋ እንደዘበት አይታይም፡፡ ሕይወትና ንብረትን በማሳጣት ብቻ አይወሰንም፡፡ ሰላም ያጣ ሕዝብና አገር ማንነቱንና ክብሩን ያጣል፡፡ የውርደት ማቅ የለበሰ፣ ለተመጽዋችነትና ለእንግልት የተዳረገ እንደሚሆን የእኛው የኋላ ታሪክ ምስክር ነው፡፡

እስኪ እንነጋገር የኢኮኖሚውን ነገር

ኢኮኖሚያችን መላ ያስፈልገዋል፡፡ በተለይ ኢኮኖሚውን በሚገባ ሊያንቀሳቅሱ የሚችሉ አሠራሮች በቶሎ መተግበር አለባቸው፡፡ ወትሮም በርካታ ችግሮችን ተሸክሞ አሁን ላይ የደረሰው የአገራችን ኢኮኖሚ በበርካታ ችግሮች ተከቦ የሚገኝ ነው፡፡

ገንቢና ግንባታ አይተዋወቁም

በግንባታ ኢንዱስትሪው ውስጥ የሚታዩት ብልሹ አሠራሮች በብዙ መንገዶች ሲገለጹ ሰምተናል፡፡ በዓይናችን የምናያቸው ደረጃቸውን ያልጠበቁ ግንባታዎች ያስከፈሉትን የሕወይትና የሀብት ኪሳራ፣ ወደፊትም ሊያስከፍሉ የሚችሉት ጉዳት እንደዘበት አይታይም፡፡

ለኮንትሮባንድ ከዛቻም ከዘመቻም የበለጠ ሥራ ያስፈልጋል

ኢኮኖሚው እንደሚፈለገው መጓዝ እንዳይችል፣ ለአገር ዕድገትና ለውጥ እንቅፋት መሆኑ እየታወቀም ከመቀነስ ይልቅ እየጦዘ የሚገኘው ሕገወጥ ንግድ፣ በኢትዮጵያ ያፈጀ ነባር ችግር መሆኑ ብቻ ሳይሆን ብሶበት መታየቱ አሳሳቢነቱን አጉልቶታል፡፡  

ቤት ሆይ ወዴት አለህ?

የመኖርያ ቤት ችግር የጥያቄ ምንጭ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ከመሠረታዊ የሰው ልጅ ፍላጎቶች የሚመደበው የመጠለያ ችግር በተለይ ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች የዘመናት ፈተና ነው፡፡

ብላሽ ግንባታ

ስለአገሪቱ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ብዙ ሲባል ኖሯል፡፡ በኢኮኖሚው ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ የያዘው ይህ ዘርፍ፣ ካለው አጠቃላይ ትይዩ ባሻገር ለአገር ሀብት ብክነትም ከፍተኛ ድርሻ አለው፡፡

‹‹እጠየቃለሁ››ን ጠበቅ!

የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከደንበኞቻቸው ወይም ከባለጉዳዮች ጋር ሊኖራቸው በሚገባው ግንኙነት ውስጥ ተጠያቂነትን ያካተተ አሠራር ይከተሉ ነበር ለማለት ይቸግራል፡፡ ጤናማ ግንኙነት አላሰፈኑም ለማለት የሚቻልባቸው በርካታ መገለጫዎች አሉ፡፡ ተቋማቱ ደንበኞቻቸውን በአግባቡ አያገለግሉም፡፡ አያስተናግዱም፡፡