Skip to main content
x

ዶልፊን

ዶልፊኖች በጣም ብሩህ አዕምሮ ያላቸው የባሕር ውስጥ አጥቢዎች ናቸው፡፡ የጥርሳም አሳ ነባሪ ዘመድ አባል ናቸው፡፡ አብዛኞቹ ዶልፊኖች በውቅያኖስ ውስጥ ሲኖሩ፣ ጥቂት የሚሆኑት ደግሞ በተለያዩ የዓለም ወንዞች ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ሥጋ በል ናቸው፡፡

አልባትሮስ

አልባትሮስ የተባለው ወፍ ‹‹በምድር ላይ በትልቅነቱ ተወዳዳሪ የሌለው ሕይወት ያለው በራሪ ማሽን›› ተብሏል ይላል ጄደብሊው ዶትኦርግ፡፡ ይህ ወፍ ክንፎቹ ከጫፍ እስከ ጫፍ ሦስት ሜትር ርዝመት ሲኖረው በሰዓት ከ115 ኪሎ ሜትር በላይ መብረር ይችላል።

200 ዓመት የሚኖሩ ኧርቺኖች

ክብና ሙሉ ለሙሉ በእሾህ የተሸፈኑት ኧርቺኖች የሚኖሩት በፖስፊክ ሐይቅ ውስጥ ነው፡፡ በተለይም ብዙም ጥልቀት በሌለው በምዕራባዊ ሰሜን አሜሪካ አካባቢ በሚገኘው የሐይቁ ክፍል ኧርቺኖች በስፋት ይኖራሉ፡፡

ንጉሡ ጥንባሳ

ንጉሥ የሚል ቅፅል የተሰጠው በደቡብ ሜክሲኮና በሰሜናዊ አርጀንቲና የሚገኘው ጥንባሳ ከ27 እስከ 32 ኢንች ይረዝማል፡፡ ከአንድ ክንፉ እስከ ሌላኛው ክንፉ ደግሞ ስድስት ጫማ ከስድስት ኢንች ይሆናል፡፡

መርዛማዋ እንቁራሪት

በደማቅ ቀለማት ያሸበረቀ ቆዳ ያላት መርዛማዋ እንቁራሪት ጣላቶቿ እንዳይነኳት ምታስጠነቅቀው በቀለሟ ነው፡፡ ለምግብነት በማይስበው ዝብርቅርቅ ቀለሟ ያልሸሿትን በአንድ ጊዜ ንክኪ ብቻ ነው ጉድ የምትሠራቸው፡፡

ባለ ሮዝ ቀለሙ አንበጣ

አረንጓዴ፣ ቡናማ አንዳንዴም ነጭ ቀለም ያላቸውን የአንበጣ ዝርያዎች እዚህም እዚያም ማየት የተለመደ ነው፡፡ ከሌሎቹ አንበጦቹ አንድ የተለየ ጂን ያለው አንበጣ ግን ጂኑ ሮዝ ቀለም አንዲኖረው አድርጎታል፡፡

ሴይጋ አንቴሎፕ

በካዛኪስታን ሜዳማ አካባቢ ላይ የሚኖረው ሴይጋ አንቴሎፕ ከዝርያዎች ልዩ የሚያደርገው አንድ ነገር አለ፡፡ አፍንጫው ያገኘውን አየር እየሳበ ወደ ውስጥ ከማስገባት ይልቅ፣ ቀዝቃዛውንም ሙቀቱንም ተቀብሎ ሙቀቱን አመጣጥኖ ነው ወደ ውስጥ የሚልከው፡፡

የዱር ድመት

ከድመት አስተኔዎች ውስጥ አንዱ የአፍሪካ የዱር ድመት ነው፡፡  በአውሮፓና እስያም ይገኛል፡፡ ዶ/ር ሰሎሞን ይርጋ ‹‹አጥቢዎች›› ባሉት መጽሐፋቸው እንደገለጹት፣ የአፍሪካ የዱር ድመት ወንዱ 5 ኪሎ ግራም፣ ሴቷ ደግሞ 4 ኪሎ ግራም ይመዝናሉ፡፡

ከወቅት ጋር ፀጉሩ የሚቀያየረው ሽኮኮ

ያማርኛ መዝገበ ቃላት ሽኮኮን ሲፈታ ያውሬ ስም፣ በጐሬ በየቋጥኙ ሥር የሚኖር የጥንቸል ዐይነት ይለዋል፡፡ በሌላ በኩል ስለዱር እንስሳት የሚያወሳ አንድ ድርሳን፣ሽኮኮን የዘራይጥ አስተኔ ይለዋል፡፡ ከተለያዩ ዝርያዎች አንዳንዱ በዛፍ ውስጥ የሚኖር፣ አንዳንዱ በመሬት ላይ የሚቆይ ዓይነት አለ ሲልም ያክላል።

እንቁራሪት

እንቁራሪት አኗኗራቸው በወንዝ አካባቢ ነው፡፡ በእንቆቅልሽ ‹‹ወንዝ ለወንዝ ሠርገኛ አረህ ላረህ ክራረኛ›› እወቅልኝ ሲባል መልሱ እንቁራሪት ይሆናል፡፡ በማንይንገረው ሸንቁጥ በተዘጋጀው ‹‹ባለአከርካሪዎች›› መጽሐፍ እንደተገለጸው፣ እንቁራሪቶች ጅራት የላቸውም፡፡