Skip to main content
x

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ተስፋና ሥጋት

በመጪው ዓመት ለሚካሄደው የቶኪዮ ኦሊምፒክ የመጀመርያ ማጣሪያውን ከማሊ አቻው ጋር መጋቢት 12 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲዮም ያደረገው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ጨዋታውን በአቻ ውጤት ማጠናቀቁ ብዙዎችን አስቆጭቷል፡፡ የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ አብርሃም መብራቱ በበኩላቸው በተጨዋቾቻቸው እንቅስቃሴ መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡ ቡድኑ ለመልሱ ጨዋታ ወደ ማሊ ባማኮ አቅንቷል፡፡ 

እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዋሊያ ቢራ ጋር አዲስ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራረመ

በኢትዮጵያ በስፖንሰርሺፕ የገበያ ድርሻ ካላቸው ተቋማት ውስጥ ቢራ በመጥመቅና በመሸጥ ላይ የሚገኙ ተቋሞች የጎላ ሚና ሲጫወቱ ቆይተዋል፡፡ ተቋማቱ ‹‹እኔ የተሻልኩ ነኝ›› የሚለውን የፕሮሞሽን ሥራዎቻቸውን ወደ ኅብረተሰቡ የሚያወርዱበት አግባብ ትውልዱን እያበላሸ መሆኑን ከግምት በማስገባት የቢራ ማስታወቂያዎች በተለይም በኤሌክትሮኒክስ መገኛኛ ብዙኃንና ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው አደባባዮች ማስታወቂያዎች እንዳይሰቀሉ በአዋጅ መከልከሉ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ያስተናገደችው የአፍሪካ ብስክሌት ሻምፒዮና በኤርትራ የበላይነት ተጠናቀቀ

የአፍሪካ ብስክሌት ኮንፌዴሬሽን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀውን አኅጉራዊ የብስክሌት ሻምፒዮና ኤርትራ፣ ኢትዮጵያና ሩዋንዳ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ስፍራ በመያዝ አጠናቀቁ፡፡ በባህር ዳር ከተማ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ በሰነበተው ውድድር 16 አገሮች የተሳተፉ ሲሆን ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሩዋንዳና ደቡብ አፍሪካ በሜዳሊያ ሰንጠረዡ ገብተዋል፡፡

ፋሲል ተካልኝ ለከፍተኛ ሥልጠና ሃንጋሪ ይገኛል

አንጋፋው የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ከተጨዋችነት እስከ አሠልጣኝነት ካፈራቸው ታላላቅ ሙያተኞች ዝርዝር ውስጥ ተካቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ምክትል አሠልጣኝ ሆኖ በማገልገል ለዓመታት አሳልፏል፡፡ አሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ በአሁኑ ወቅት ደግሞ የዓለም አቀፍ ኢሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) በየዓመቱ ለአባል አገሮች በሚሰጠው የኦሊምፒክ ሶሊዳሪቲ አማካይነት ለከፍተኛ የእግር ኳስ አሠልጣኝነት ሥልጠና ወደ ሃንጋሪ አምርቷል፡፡

አለመደማመጥና አለመተማመን ፈተና የሆነበት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከአገር አቀፍ የስፖርት አስተዳደር ሥራዎቹ ባሻገር በአኅጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሚመለከቱ ውሳኔዎች ላይ የኢትዮጵያን ጥቅም በሚያስጠብቅ አኳኋን የመሳተፍ፣ ድምፅን የማሰማት ኃላፊነት እንዳለበት ይታመናል፡፡

የኢትዮጵያ ቡድን ለዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና መሰናዶ ጀምሯል

የዓለም አገር አቋራጭ አትሌቲክስ ውድድር መጋቢት 21 ቀን 2011 ዓ.ም. በዴንማርክ አርሁስ ከተማ ይጀመራል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ ለቅድመ ዝግጅቱ ይረዳው ዘንድ 36ኛው የጃንሜዳ አገር አቋራጭ ውድድር ያከናወነ ሲሆን፣ ከፍተኛ ውጤት ያላቸውና የዕድሜ ተገቢነት ያሟሉ አትሌቶች ተመርጠው ዝግጅት ጀምረዋል፡፡ ከ6 ኪሎ ሜትር ርቀት ጀምሮ እስከ 10 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍነውን ውድድር ያሰናዳው ፌዴሬሽኑ፣ በርካታ ልምድ ያላቸውን አትሌቶች መልምሎ በአዲስ አበባ ስታዲዮም እንዲሁም በጫካ ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል፡፡

የእግር ኳስ አመራሮችን ለሁለት የከፈለው የሪፎርም ትግበራ ቅሬታ አስነሳ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ራሱን ለማደስ ባደረገው ሁሉ አቀፍ ጥረት መሠረታዊ ችግሮቹንና ድክመቶቹን መለየቱን አስታውቋል፡፡ ለመሠረታዊ ለውጥ ትግበራው መነሻ ጥናት ለማድረግም ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ማውጣቱ ሲነገር ቆይቷል፡፡

የቴክኒክ ክፍሉ የእግር ኳስ ልማት ውጥኖች

የጠራ ተቋማዊ አደረጃጀት ሳይኖረው ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ የምሥረታ ዕድሜ ካላቸው ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች መካከል አንዱ ቢሆንም፣ እንደ አለመታደል ሆኖ ከእነ ችግሮቹ ዛሬም በእኔነት ስሜት የሚብሰለሰሉለት ተመልካቾች አላጣም፡፡ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሁሉም የክልል ከተሞች በክብረ በዓል መልክ የሚከበረውን የብሔር ብሔረሰቦች ዓመታዊ ዝግጅት ተከትሎ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ስታድየሞች መገንባታቸው ለእግር ኳሱ ተደራሽነት የጎላ ድርሻ እንዳለው የሚናገሩ አሉ፡፡

ዋሊያዎቹ በሙያተኞች አተያይ

ከሦስት አሠርታት በኋላ እ.ኤ.አ በ2012 (ጥቅምት 2005 ዓ.ም.) ለአፍሪካ ዋንጫ ብቅ ብሎ ሳይታሰብ በዚያው የጠፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ከአህጉራዊ ተሳትፎ ከራቀ ሰባት ዓመታትን ሊያስቆጥር ነው፡፡