Tag: ሙዚየም
የእንግሊዝ ሙዚየሞች ከመቅደላ የዘረፉትን ቅርሶች ለመመለስ ምን ያህል ዝግጁ ናቸው?
ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ከ152 ዓመታት በፊት መቅደላ ላይ ከተሰዉ በኋላ ከአምባው የደረሰው በጄኔራል ናፒር የሚመራው የእንግሊዝ ጦር ወደ አገሩ ባዶ እጁን አልተመለሰም፡፡ መቅደላ አምባ በንጉሠ ነገሥቱ ቴዎድሮስ በተደራጀው ሙዚየም ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ውድ ቅርሶችን ዘርፎ እንጂ፡፡
የተስፋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኢትኖግራፊክ ሙዚየም
የሰባት አሠርታት ዕድሜ ያስቆጠረው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ካሉት በርካታ ተቋማት አንዱ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ነው፡፡
ከሦስት ዓመታት በፊት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ ያከበረውና በራስ መኰንን ስም በሚጠራው ሕንፃ የሚገኘው ተቋሙ ካቀፋቸው ልዩ ልዩ ክፍሎች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱት የአገር ውስጥና የውጭ ቋንቋዎች አብያተ መጻሕፍትና የኢትኖግራፊክ ሙዚየም ናቸው፡፡
የዳግማዊ አፄ ምኒልክ ቤተ መንግሥት ጥገና ተጓተተ
እንጦጦ ላይ በ1875 ዓ.ም. የተቋቋመውና በጊዜ ብዛት አርጅቶ ሊፈራርስ የተቃረበው የዳግማዊ አፄ ምኒልክ ቤተ መንግሥት የቀድሞ ቅርፅና ይዘቱን ሳይለቅ የመጠገኑ ሥራ በመጓተቱ ሕንፃው ለበለጠ ጉዳትና አደጋ መጋለጡ ተገለጸ፡፡
በብሔራዊ ሙዚየም የሚቀመጡት ቅርሶች የትኞቹ ናቸው?
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ቅጥር ውስጥ ከሚገኙ ሐውልቶች መካከል በአንድ ጥግ አፄ ኃይለ ሥላሴ ተማሪዎችን ሲያነጋግሩ የሚያሳየው፣ በሌላው ኢትዮጵያዊ የዘር ግንድ እንዳለው የሚነገርለት የአሌክሳንደር ፑሽኪን፣ የአዘቲክስን (ሜክሲኮ) የጥንት ሥልጣኔ የሚያሳየው የኦልማክ ሐውልት ይገኛል፡፡ ወረድ ብሎ ደግሞ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አልባኒያውያንን እንደጨፈጨፈ የሚነገርለት የኮሚኒስቱ ኢንቨር ሆዛ ሐውልት ከአንዱ ግርጌ አለ፡፡
ባልና ሚስቱ የኮርያ ዘማቾች ለሙዚየም ስጦታ አበረከቱ
ከዛሬ 60 ዓመት በፊት በኮርያ ልሳነ ምድር ዘምተው ዓለም አቀፍ ግዳጃቸውን የተወጡ ባልና ሚስት ይገለገሉባቸው የነበሩ ልዩ ልዩ ዕቃዎችን ለኮርያ ዘማቾች ማኅበር ሙዚየም ታኅሣሥ 17 ቀን 2010 ዓ.ም. በስጦታ አበረከቱ፡፡
Popular