Wednesday, March 29, 2023

Tag: ማራቶን

የቀነኒሳ በቀለ ቅሬታና የቶኪዮ ኦሊምፒክ ማጣሪያ

ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ባስከተለው የጤና ሥጋት ሳቢያ በርካታ ዓለም አቀፍ ክንውኖች እንዳይካሄዱ ተስተጓጉለዋል፣ አሊያም ተሰርዘዋል፡፡ ዓምና መካሄድ የነበረበት የቶኪዮ ኦሊምፒክ ወደ ዘንድሮ ተሸጋግሮ አገሮች ተሳታፊ አትሌቶቻቸውን በማዘጋጀት ላይ ይገኛሉ፡፡

ኢትዮጵያውያን በድል የደመቁበት ቫሌንሲያ ማራቶን

ባለፈው ሳምንት በተለያዩ አገሮች በርካታ የጎዳና ላይ ውድድሮች ተከናውነዋል፡፡ ወርልድ አትሌቲክስ በወርቅ ደረጃ ዕውቅና ከሚሰጣቸው የጎዳና ላይ ውድድሮች መካከል በስፔን ቫሌንሲያ የተደረገውን የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያኑ በሁለቱም ፆታ አሸናፊዎች ሆነዋል፡፡ በወንዶች ክንዴ አጥናው የወርቅ ሜዳሊያውን በማጥለቅ የቦታው ክብረ ወሰን ማስመዝገብ የቻለበትን ድል አስመዝግቧል፡፡

የቶኪዮ ኦሊምፒክ ማራቶን ሐሩሩን ፍራቻ በሳፖሮ ከተማ ይካሄዳል

በመጪው ሐምሌ የሚካሄደው የ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ጦስ ምክንያት ከወዲሁ ሥጋት አጥልቶበታል፡፡ የኦሊምፒክ ውድድሩ የሚከናወንባት ዋና ከተማዋ ቶኪዮ በበጋ ወቅቷ ሊያጋጥማት የሚችለው ከፍተኛ የሙቀት መጠንና ወበቅ ሥጋት ይሆንበታል ተብሎ የሚታሰበውን ዕርምጃን ጨምሮ የማራቶን ውድድሮችን በተለዋጭ ከተሞች እንዲካሄዱ፣ ከዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ) የቀረበላትን ሐሳብ መቀበሏ ታውቋል፡፡

ለኬንያ ብስራት ለኢትዮጵያ ሥጋት የሆነው የሰሞኑ የአትሌቲክስ ድል

ኬንያውያን አትሌቶች ባለፈው ሳምንት መገባደጃ በድርብ ድል ተንበሽብሸዋል፡፡ ታዋቂው የማራቶን አውራ ኢልዩድ ኪፕቾጌ ታሪካዊ የተሰኘውን ውጤት በማስመዝገብ ዓለምን አስደምሟል፡፡ በሴቶችም ለ16 ዓመታት በእንግሊዛዊቷ ፓውላ ራድክሊፍ ተይዞ የቆየው የርቀቱ ክብረወሰን በቢርጊድ ኮስጄይ አማካይነት መሰበሩ ለኬንያውያን ብስራት ሲሆን ለኢትዮጵያውያን ደግሞ ሥጋት ሆኗል፡፡

ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ተስፋ የተጣለበት ሙስነት ገረመው

የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ) በወርቅ ደረጃ ከሚመድባቸው የጎዳና ውድድሮች የለንደን ማራቶን ተጠቃሽ ነው፡፡ ከተመሠረተ አራት አሠርታት ያስቆጠረው ለንደን ማራቶን እንግሊዛውያን ከማንነታቸው ጋር የሚያይዟቸውን ታሪካዊ ቅርሶቻቸውን ለዓለም ሕዝብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚያስተዋውቁበት መድረክ እንደሆነ ይታመናል፡፡

Popular

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...

Subscribe

spot_imgspot_img