Tag: ማራቶን
በርሊን ያነገሠችው የኤልዶሬት አካዴሚ ፍሬ ኤሊዩድ ኪፕቾጌ
የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ) በወርቅ ደረጃ ከሚመድባቸው ማራቶን ተጠቃሽ ነው፡፡ አሸናፊዎች ረብጣ ዶላር የሚያሳፍሰው ዓመታዊው የበርሊን ማራቶን ባለፈው እሑድ ሲከናወን በሁለቱም ጾታ በኬንያውያን አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ሩጫና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዱባይ ማራቶን
ዓርብ ጥር 18 ቀን 2010 ዓ.ም. የተባበሩት ዓረብ ኤምሬት ዱባይ አውራ ጎዳናዎች በኢትዮጵያውያንና ከፍ ብሎ በተውለበለው ሰንደቃቸው ጎልተው የታዩበት ክስተት ዕውን ሆኗል፡፡ ዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤፍ) በወርቅ ደረጃ ከሚመድባቸው ዓመታዊ የማራቶን ውድድሮች አንዱ እንደሆነ በሚነገርለት ዱባይ ማራቶን፣ ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች በሁለቱም ፆታ ለውድድሩ የተዘጋጀውን ሜዳሊያና የገንዘብ ሽልማት ጠራርገው የግላቸው በማድረግ ብቃታቸውን ለዓለም አሳይተዋል፡፡ በወንዶች ሙስነት ገረመው፣ በሴቶች ደግሞ ሮዛ ደረጀ የወርቅ ሜዳሊያውን በመውሰድ ቀዳሚዎች ሆነዋል፡፡
ሁለቱ የረዥም ርቀት ባለታሪኮች በለንደን ማራቶን ሊገናኙ ነው
በረዥም ርቀት በማይታመን ብቃትና ፍጥነት በአሸናፊነቱ የሚታወቀው ቀነኒሳ በቀለ ሚያዝያ 14 ቀን 2010 ዓ.ም. በሚካሄደው ለንደን ማራቶን ከእንግሊዛዊው ሞ ፋራህና ከኬንያዊው ኤሉዱ ኪብቾጌ ጠንካራ ፉክክር ይጠብቀዋል፡፡ በሌላ በኩል ለበርካታ ጊዜያት ከአትሌቲክሱ መድረክ ርቃ የከረመችው መሠረት ደፋር የመጀመርያዋን የማራቶን ሩጫ በቶኪዮ እንደምታደርግ የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማኅበር (አይኤኤኤፍ) ዘገባ አመልክቷል፡፡
የረዥም ርቀት ንግሥቷ በማራቶንም ብቃቷን ማሳየት ጀመረች
ለዓመታት የረዥም ርቀት ንግሥነቷን አስጠብቃ የቆየችው ጥሩነሽ ዲባባ በዓለም አቀፍ የሩጫ ውድድር ገድሏ መዘከር የጀመረው ከ18 ዓመት ዕድሜዋ ጀምሮ ነው፡፡ በብዙ ዓለም አቀፍ መድረኮች ወድቃ በመነሳትና ከሕመም ጋር በመታገል ከኋላ ተነስታ ያሸነፈችባቸው የዓለም ሻምፒዮናና ኦሊምፒኮች ምስክሮች ናቸው፡፡
Popular
በሕገ መንግሥቱ የተዋቀረው ‹‹የብሔር ፖለቲካ›› እና ‹‹ሥርዓቱ›› ያስከተለው መዘዝና መፍትሔው
(ክፍል አራት)
በዓቢዩ ብርሌ (ጌራ)
ባለፈው ጽሑፌ (በክፍል ሦስት) አሁን ያለው...
ለመጪው ዓመት የሚያስፈልገው 4.3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነዳጅ 4.4 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይጠይቃል
ለመጪው 2016 ዓ.ም. ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ለታቀደው 4.3...