Tag: ሪል ስቴት
የውጭ ሪል ስቴት ኩባንያዎች ከፍተኛ ዋጋ ማቅረባቸው እያነጋገረ ነው
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰፊው ሕዝብ ተጠቃሚ ያደርጋል ያለውን የቤት ልማት መርሐ ግብር በመንግሥትና በግል ባለሀብቶቹ የጋራ ልማት ማስኬድ መጀመሩን በማስመልከት ከውጭ አልሚዎች ጋር እየሠራ ቢሆንም፣ በሪል ስቴት ኩባንያዎች የሚቀርበው ከፍተኛ ዋጋ ግን አሳሳቢ መሆኑ እየተገለጸ ነው፡፡
የቤት ፈላጊዎችን መብት ለማስከበር በሪል ስቴት አልሚዎች ላይ ግዴታ የሚጥልና ቁጥጥር የሚያደርግ ሕግ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊቀርብ ነው
የሪል ስቴት አልሚዎችን የሚቆጣጠርና የቤት ፈላጊ ደንበኞቻቸውን መብት የሚያስከበር የተለያዩ ግዴታዎችን የሚጥል ረቂቅ ሕግ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መላኩን፣ ሪፖርተር ያገኘው መረጃ አመለከተ፡፡
ለጋራ ቤቶች ግንባታ አዲስ አማራጭ ይዞ የመጣው ድርጅት ከወዲሁ ሁለት ሚሊዮን ካሬ ሜትር ቦታ ማዘጋጀቱን አስታወቀ
ጎጆ ማርኬቲንግ ሰርቪስ የተሰኘውን ድርጅት በሥራ አስኪያጅነት የሚመሩትና “ቤዝ ሶሉሽን ፕሮጀክት” የሚል ስያሜ የተሰጠውን የጋራ ቤቶች ልማት በግለሰቦች ይዞታ ላይ በስምምነት ለመገንባት የታቀደበትን ሐሳብ ያመነጩት ግለሰብ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በትብብር ለሚካሄደው የቤት ግንባታ ሥራ ከ1,700 ባለይዞታዎች ሁለት ሚሊዮን ካሬ ሜትር ቦታ ከወዲሁ መሰባሰቡን አስታወቁ።
ኖኅ ሪል ስቴት ሙሉ ለሙሉ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ባለ 36 ወለል ሕንፃ በ1.6 ቢሊዮን ብር እንደሚገነባ አስታወቀ
ኖኅ ሪል ስቴት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ለገሐር አካባቢ ባለ 36 ወለል ለቢሮ ተቋማት የሚሆን ሕንፃ ሊገነባ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ይህ የተገለጸው በተለምዶ ፊጋ እየተባለ በሚጠራውና ሰሚት አካባቢ በሚገኘው መንደር ‹‹ኖኅ ጋርደን የመኖሪያ አፓርትመንቶች›› እሑድ ግንቦት 25 ቀን 2011 ዓ.ም. ለቤት ገዥዎች በተላለፉት ወቅት ነው፡፡
ኖህ ሪል ስቴት የገነባቸውን ቤቶች ለማስረከብ የውኃና የመብራት ችግር ተጋርጦብኛል አለ
ኖህ ሪል ስቴት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በርካታ መኖሪያ ቤቶችን በመገንባት ውጤታማ ሥራ ቢያከናውንም፣ የመብራትና የውኃ አቅርቦት ችግር ሊቀረፍለት እንዳልቻለ ገለጸ::
Popular