Wednesday, July 24, 2024

Tag: ርዕሰ አንቀጽ

በብሔራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት የሚቻለው ሴረኝነት ሲመክን ነው!

በሁሉም ብሔራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት ባይቻልም፣ መሠረታዊ በሚባሉት ላይ ግን መግባባት አያቅትም፡፡ ሊያግባቡ ከሚችሉ በጣም መሠረታዊ ከሚባሉ ጉዳዮች መሀል በዋነኝነት የሚጠቀሱት ሰብዓዊነት፣ ፍትሐዊነት፣ እኩልነትና ነፃነት ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ምድር የማንነት፣ የእምነት፣ የቋንቋ፣ የባህል፣ የፆታ፣ የፖለቲካ አቋምና የመሳሰሉት ፀጋዎች ተከብረው በሰላም መኖር ይቻላል፡፡

ሰብዓዊነትን የሚገዳደረው ጭካኔ በሕግ መቆም አለበት!

ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸሙ ያሉ ኢሰብዓዊ ጭካኔዎችና ወንጀሎች ገደባቸውን እያለፉ ነው፡፡ ከሰውነት ደረጃ የወረዱ አውሬያዊ ባህሪያት ሰው የመሆን ፀጋን እየገፈፉ ነው፡፡ በአደባባይ ሰብዓዊ ፍጡርን ዘቅዝቆ መስቀል፣ በጭካኔ መግደል፣ ማሰቃየት፣ ማፈናቀል፣ አስገድዶ መድፈርና የመሳሰሉት ነውረኛ ድርጊቶች ተባብሰው ቀጥለው የሰው ልጅን ከእነ ሕይወቱ እሳት ውስጥ መክተት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡

ግብታዊ ዕርምጃ የኑሮ ውድነቱን አያረግብም!

በአሁኑ ጊዜ በምግብና ምግብ ነክ በሆኑ መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ የሚስተዋለው ከመጠን ያለፈ የዋጋ ጭማሪ፣ የሸማቾችን የመግዛት አቅም በማዳከም የኑሮ ውድነቱን እያባባሰው ነው፡፡

ታላቁ የዓድዋ ድልና የዘመኑ ትውልድ ፈተና!

ታላቁ የዓድዋ ድል 126ኛ ዓመት ሲዘከር የጀግኖቹ ኢትዮጵያውያን ተጋድሎ መታወስ የሚኖርበት፣ ለአገራቸው ከነበራቸው ጥልቅ ፍቅርና ለዘመናት ከገነቡት ታላቅ የሞራል ልዕልና ጋር ነው፡፡ አፍሪካንና ሌሎች አካባቢዎችን እንደ ቅርጫ ለመቀራመት ከተነሱት የዘመኑ ቅኝ ገዥዎች ኢትዮጵያውያን ጀግኖች አገራቸውን መካላከል የቻሉት፣ ከአገራቸው በፊት የሚቀድም አንዳችም ፍላጎት እንደሌለ ለመረዳት የሚያስችል ዕፁብ ድንቅ የሆነ ሞራላዊ እሴት ስለነበራቸው ነው፡፡

ታላቁን ግድብ የገነባ ትውልድ በአገር ጉዳይ መነጋገር አያቅተውም!

የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ሲበሰር፣ በኢትዮጵያውያን ዘንድ የተፈጠረው የዘመናት ቁጭት የተላበሰ ወደር የሌለው ደስታ ነው፡፡ ይህ ደስታ ወደ ውስጥ የሚፈስ ዕንባን ዋጥ የሚያስደርግ ብቻ ሳይሆን፣ ተባብሮ መሥራት ከተቻለ ተዓምር መፍጠር የሚያስችል ዕምቅ አቅምን የሚያወጣ እልህ ጭምር የተላበሰ ነው፡፡ ይህ እልህ የዓባይ ውኃ ለዘመናት ለምን ሲፈስ ዝም ብለን ስናየው ኖርን አሰኝቶ፣ በርካታ ግድቦችን ለመገንባት ምንም የሚሳን ነገር እንደሌለም ማሳያ ነው፡፡ ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ለምን ጨለማ ውስጥ ሆነው የድህነት መጫወቻ ሆኑ የሚለው የዘመናት ቁጭት፣ ‹‹ዓባይ ማደሪያ የለው ግንድ ይዞ ይዞራል›› ከሚለው ዕድሜ ጠገብ ምሳሌያዊ አባባል ጋር ማክተም ይኖርበታል፡፡

Popular

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...

ግለሰብ ነጋዴዎችን በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ለማድረግ ያለመው ረቂቅ አዋጅ ተከለሰ

በምትኩ የንግድ ተቋማት በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ይሆናሉ...

አሳርና ተስፋ!

ከቱሉ ዲምቱ ወደ ቦሌ ጉዞ ልንጀምር ነው፡፡ ገና ከመንጋቱ...

የአገሪቱን የፖለቲካ ዕብደት ለማርገብ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ሚና ምን ይሁን?

በያሲን ባህሩ   የኦሮሚያ ብልፅግና      በአገር ደረጃ የብሔር ፖለቲካ በሥራ...

Subscribe

spot_imgspot_img