Tag: ስኳር ኮርፖሬሽን
የስኳር ኮርፖሬሽን ቦርድ ሜቴክ እጅ የቀሩ ሦስት የስኳር ፕሮጀክቶች ኮንትራት እንዲቋረጥ ወሰነ
የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ለዓመታት ሊያጠናቅቃቸው ያልቻላቸው ሦስት ግዙፍ የስኳር ፕሮጀክቶች የግንባታ ውሎች እንዲቋረጡ መወሰኑን፣ የፕሮጀክቶቹ ባለቤት የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡ ይኼንኑ ውሳኔም ኮርፖሬሽኑን የሚመራው ቦርድ እንዳፀደቀው ተገልጿል፡፡
ስኳር ኮርፖሬሽን ሜቴክ በያዛቸው ፕሮጀክቶች ላይ ዕርምጃ እንዳይወስድ በከፍተኛ አመራሮች ዛቻና ማስፈራሪያ ይደርሰው እንደነበር ገለጸ
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የያዛቸውን አንዳንድ የስኳር ፕሮጀክቶች ውል በማቋረጥ ለማስቆም ሲሞከር የፕሮጀክቱን ባለቤት የስኳር ኮርፖሬሽን አመራሮች፣ ‹‹ይህ ማለት ከግንብ ጋር መጋጨት ነው፣ ወዮላችሁ አርፈችሁ ተቀመጡ፤›› የሚሉ ዛቻና ማስፈራሪያዎች ሲደርሷቸው እንደነበር ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ እንዳወቅ አብቴ ይፋ አደረጉ።
ክሳቸው ያልተቋረጠ ተከሳሾች ቤተሰቦች አቤቱታቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማቅረባቸውን ቀጥለዋል
መንግሥት ይቅርታ በማድረግና ክስ በማቋረጥ ከግንቦት 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ከ771 በላይ እስረኞች እንዲፈቱ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ፣ ክሳቸው ያልተቋረጠላቸው በርካታ እስረኞች ቤተሰቦች አቤቱታቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማቅረባቸውን ቀጥለዋል፡፡
ክሳቸው ከተቋረጠው የሙስና ወንጀል ተጠርጣሪዎች ጋር ታስረው የነበሩ ተከሳሾች ቅሬታቸውን ለመንግሥት አቀረቡ
የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር በአዋጅ የተሰጣቸውን ሥልጣን በመጠቀም በሙስና፣ በሽብርና በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው የተከሰሱና ክርክራቸውን ጨርሰው ተፈርዶባቸው የነበሩ ግለሰቦች እንዲለቀቁ ሲያደርጉ፣ በተመሳሳይ ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ በርካታ እስረኞች መታለፋቸው ቅሬታ እንዳደረባቸው ለመንግሥት አቤቱታቸውን አቀረቡ፡፡
በሙስና ምክንያት የታሰሩ ተከሳሾች ቤተሰቦች ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ አቤቱታ አቀረቡ
የልጆቻቸውን የትምህርት ቤትና የቤት ኪራይ መክፈል እንዳልቻሉ የሚናገሩ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸውና በማረሚያ ቤት የሚገኙ የስኳር ኮርፖሬሽን የተወሰኑ ታሳሪዎች ቤተሰቦች፣ በቅርቡ ለተሾሙት የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቤቱታ አቀረቡ፡፡ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬም በአግባቡ ተቀብለውና አቤቱታቸውን ሰምተው ምላሽ እንደሚሰጧቸው በመንገር መልሰዋቸዋል፡፡
Popular