Tag: ስኳር ኮርፖሬሽን
በሙስና ምክንያት የታሰሩ ተከሳሾች ቤተሰቦች ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ አቤቱታ አቀረቡ
የልጆቻቸውን የትምህርት ቤትና የቤት ኪራይ መክፈል እንዳልቻሉ የሚናገሩ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸውና በማረሚያ ቤት የሚገኙ የስኳር ኮርፖሬሽን የተወሰኑ ታሳሪዎች ቤተሰቦች፣ በቅርቡ ለተሾሙት የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቤቱታ አቀረቡ፡፡ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬም በአግባቡ ተቀብለውና አቤቱታቸውን ሰምተው ምላሽ እንደሚሰጧቸው በመንገር መልሰዋቸዋል፡፡
የቀድሞ የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስትር በስኳር ኮርፖሬሽን ተጠርጣሪዎች ላይ ምስክር ሆነው ቀረቡ
በሚኒስትር ማዕረግ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አማካሪና የቀድሞ የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስትር፣ ዓቃቤ ሕግ በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ በመሠረተባቸው በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሸን የኦሞ ኩራዝ 5 ስኳር ፕሮጀክት ተጠርጣሪዎች ላይ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጡ፡፡
ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የኤታኖል ፋብሪካ ሊገነባ ነው
የኢትዮጵያ ማዕድን፣ ነዳጅና ባዮፊውል ልማት ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር በ1.1 ቢሊዮን ብር ወጪ የኤታኖል ፋብሪካ ሊገነባ ነው፡፡ የኤታኖል ፋብሪካው የሚገነባው በደቡብ ኦሞ ኩራዝ ሦስት የስኳር ፋብሪካ ሲሆን፣ ኤታኖሉ የሚመረተው ከኩራዝ አንድና ኩራዝ ሦስት የሚወጣውን ሞላሰስ በማጣራት እንደሆነ ታውቋል፡፡
የግሉ ዘርፍ በባዮፊዩል ልማት እንዲሳተፉ ተጠየቀ
በባዮፊውል ልማት የግሉ ዘርፍ ከመንግሥት ጋር ተባብሮ እንዲሠራ ጥሪ ቀረበ፡፡ የአቪዬሽን ባዮፊውል ጉባዔ ማክሰኞ መጋቢት 11 ቀን በሒልተን ሆቴል ሲካሄድ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ መብራህቱ መለስ (ዶ/ር)፣ መንግሥት የባዮፊውል ልማት በሰፊው ለመሥራት ከፍተኛ ቁርጠኝነት እንዳለው ገልጸዋል፡፡ የግሉ ዘርፍ ከመንግሥት ጋር ተባብሮ እንዲሠራ ፍላጎት እንዳለውም ጠቁመዋል፡፡
2.5 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር የሚያመርተው ኦሞ ኩራዝ ሁለት ፋብሪካ ሥራ ጀመረ
ከ6.67 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደወጣበት የተገለጸው የኦሞ ኩራዝ ሁለት ስኳር ፋብሪካ የምርት ሥራ መጀመሩ ተገለጸ፡፡
ባለፈው ዓመት ፋብሪካው የምርት ሙከራ ጀምሮ ነበር፡፡ ሆኖም በድንገተኛ ዝናብ ምክንያት ሙከራው ቢቋረጥም፣ ከታኅሳስ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ማምረት እንደጀመረ የስኳር ኮርፖሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ጋሻው አይችሉህም ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ፋብሪካው መጋቢት 14 ቀን 2009 ዓ.ም. የሙከራ ምርት መጀመሩ ይታወሳል፡፡
Popular
[ክቡር ሚኒስትሩ አምሽተው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው ‹‹ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ሕዝባችንን እናሻግራለን›› የሚለውን የቴሌቪዥን ዜና ተመልክተው ለብቻቸው ሲስቁ አገኟቸው]
ስልክ እያወራሽ ነበር እንዴ?
ኧረ በጭራሽ... ምነው?
ታዲያ ምንድነው ብቻሽን የሚያስቅሽ?
አይ......
ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ
የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል
የሐበሻ ቢራ...
የባንኮች ብድር አሰጣጥ ፍትሐዊና ብዙኃኑን ያማከለ እንዲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ
ባንኮች የብድር አገልግሎታቸውን በተቻለ መጠን ፍትሐዊ፣ የብዙኃኑን ተጠቃሚነት ያማከለና...