Tag: ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር
ለእግር ኳሱ ብሎም ለህልውናው የሚሰበከው ሰላም
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከደርቢ ጨዋታዎች የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ ቡና ክለቦች የሚያደርጉት ግጥሚያ ይጠቀሳል፡፡ እሑድ፣ ታኅሣሥ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም የተከናወነው የሁለቱ ቡድኖች ግጥሚያ በሌሎች አገሮች ከሚታዩ ደርቢዎች አንፃር ሲታይ ሚዛን ባይደፋም፣ እንደ አንጋፋ ተቀናቃኝነታቸው፣ እንደ ደጋፊዎቻቸው ብዛትና ንቃት ብዙ የተጠበቀው ጨዋታ ጉጉትን ቢያኮስስም፣ በዕለቱ የተላለፈው መልዕክት ግን በሰላም ዕጦት መደበኛ መርሐ ግብራቸውን ማከናወን ለተሳናቸው በርካታ ክለቦች የጎላ ፋይዳ እንዳለው ታይቷል፡፡
‹‹ለስፖርታዊ ጨዋነት መጓደልና ውጤት መጥፋት ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ተጠያቂ ናቸው›› የፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ
በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ስፖርታዊ ውድድሮች የሰላምን እሴቶች ጠብቀው መከናወን ይችሉ ዘንድ ስፖርት ኮሚሽንና ብሔራዊ ፌደሬሽኖች የተቀናጀ ሥራ መሥራት እንዳለባቸው የሴቶች፣ ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጠይቋል፡፡
የአፄ ቴዎድሮስ 150ኛ ዓመት መታሰቢያ
ከዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ጋር ስማቸው አብሮ የሚነሳው አፄ ቴዎድሮስ በአኃዳዊ የአገዛዝ ሥርዓት አገሪቷን ያስተዳደሩ መሪ ናቸው፡፡ በትውልድ ስማቸው ካሳ ኃይሉ፣ በፈረስ ስማቸው አባ ታጠቅ፣ በወታደራዊ ስማቸው መይሳው ካሳ እንዲሁም አንድ ለእናቱ የተባሉ የአፄውን የተለያዩ ማንነቶች የሚያንፀባርቁ ስያሜዎች ናቸው፡፡ የተወለዱትም አገሪቷ በባላባቶች ተከፋፍላ በምትመራበት በዘመነ መሳፍንት ወቅት ነበር። አባታቸው ደጃዝማች ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ የቋራ ገዢ ነበሩ።
ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ማገዱ ተሰማ
የኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ላለፉት ዘጠኝ ወራት የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅትን በዋና ዳይሬክተር ሲመሩ የቆዩትን አቶ ዮሐንስ ጥላሁን ከሰኞ የካቲት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ከሥራ እንዳገደ ተሰማ፡፡ ምክትላቸው አቶ የቻለ ምሕረት ድርጅቱን በውክልና እያስተዳደሩ እንዲቆዩ ወስኗል፡፡
የቱሪዝም ድርጅት ኃላፊ ‹‹ከሕግ ውጪ ሁለት ደመወዝ›› በመቀበልና በአስተዳደር ድክመት እንዲከሰሱ ተጠየቀ
የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅትን ላለፉት ዘጠኝ ወራት በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ዮሐንስ ጥላሁን፣ መንግሥት ከመደበላቸው ደመወዝ በተጨማሪ በየወሩ ስምንት ሺሕ ዶላር ከሕግ ውጪ ሲቀበሉ እንደነበር በማስታወቅ በሕግ ሊጠየቁ ይገባል ሲል የድርጅቱ ቦርድ ጥያቄ አቀረበ፡፡
Popular
[ክቡር ሚኒስትሩ አምሽተው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው ‹‹ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ሕዝባችንን እናሻግራለን›› የሚለውን የቴሌቪዥን ዜና ተመልክተው ለብቻቸው ሲስቁ አገኟቸው]
ስልክ እያወራሽ ነበር እንዴ?
ኧረ በጭራሽ... ምነው?
ታዲያ ምንድነው ብቻሽን የሚያስቅሽ?
አይ......
ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ
የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል
የሐበሻ ቢራ...
የባንኮች ብድር አሰጣጥ ፍትሐዊና ብዙኃኑን ያማከለ እንዲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ
ባንኮች የብድር አገልግሎታቸውን በተቻለ መጠን ፍትሐዊ፣ የብዙኃኑን ተጠቃሚነት ያማከለና...