Sunday, April 21, 2024

Tag: ንግድ ሚኒስቴር

በተያዘው በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ 4.43 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቀደ

በተያዘው አዲሱ የ2011 በጀት ዓመት የተሻለ ሰላምና መረጋጋት ይሰፍናል ተብሎ በመታመኑ፣ የፌዴራል መንግሥት ከወጪ ንግድ ዘርፍ 4.43 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ዕቅድ አወጣ፡፡

ንግድ ሚኒስቴር በፓልም ዘይት ንግድ ለሚሰማሩ ረቂቅ መመርያ አዘጋጀ

ንግድ ሚኒስቴር ከውጭ ፓልም ዘይት አስመጥተው ማከፋፈል የሚፈልጉ ኩባንያዎችን ማስተናገድ የሚያስችል ረቂቅ መመርያ አዘጋጀ፡፡ በተዘጋጀው ረቂቅ መመርያ ላይ ንግድ ሚኒስቴር ከክልልና ከተማ አስተዳደር፣ ከመንግሥት፣ ከኢንዶውመንትና ከግል ድርጅቶች ጋር መክሯል፡፡

የሚያነቅፈው የወጪ ንግድና አዲሱ አመራር

የአገሪቱ የወጪ ንግድ የሚጠበቅበትን ያህል ገቢ ሊያስገኝ አልቻለም፡፡ እንዲያስገኝ የታቀደውን ብቻም ሳይሆን፣ ከዚህ ቀደም ሲያስገኝ የነበረውን የውጭ ምንዛሪ ገቢ ማስገኘት ተስኖት ማሽቆልቆል ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡

የዘጠኝ ወራት የወጪ ንግድ ገቢ 2.1 ቢሊዮን ዶላር ሆነ

ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ 2.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ፡፡ ይህ ገቢ በዕቅድ ተይዞ ከነበረው 3.6 ቢሊዮን ዶላር ጋር ሲነፃፀር 57 በመቶው ብቻ እንደተሳካ ታውቋል፡፡ በተጨማሪም ካለፈው ዓመት የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ጋር ሲነፃፀር የ4.3 በመቶ (100 ሚሊዮን ዶላር) ብቻ ጭማሪ ተመዝግቧል፡፡ አብዛኛው ገቢ ከዚህ ቀደም እንደተለመደው ከግብርናው ዘርፍ የተገኘ ሲሆን፣ ቀሪው ከማኑፋክቸሪንግና ከማዕድን ዘርፍ ነው፡፡

የንግድ ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ዛሬ ይፋ ይደረጋል

ንግድ ሚኒስቴር የአገሪቱን አጠቃላይ የዘጠኝ ወራት የወጪና ገቢ ንግድ አፈጻጸም ሪፖርት ለማሳወቅ ለረቡዕ ግንቦት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ቢይዝም፣ ከቡና ወጪ ንግድ የተመዘገበው የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ይፋ ተደርጓል፡፡  በ2010 በጀት ዓመት ከሐምሌ እስከ መጋቢት ወራት ውስጥ የታየው የቡና የወጪ ንግድ አፈጻጸምን በማስመልከት የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ግብይትና ልማት ባለሥልጣን ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያሳየው ለውጭ ገበያ ከቀረበው ቡና የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ 560.24 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡  

Popular

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...

የአገሪቱ ባንኮች የመጭበርበር ተጋላጭነት እየጨመረ መሆኑን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ

በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ2 ቢሊዮን ብር መጭበርበሩን ገልጿል ቀሲስ በላይ...

Subscribe

spot_imgspot_img