Tag: ንግድ
ኢትዮጵያ ያፀደቀችው የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ማስጀመርያ ቀን በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ ተራዘመ
ኢትዮጵያ በመጋቢት ወር 2011 ዓ.ም. በፓርላማ አፀድቃ አባል የሆነችበት የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ይጀመራል ተብሎ ከተጠበቀበት ሚያዝያ 2 ቀን 2012 ዓ.ም.፣ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማን ከጎዳና ንግድ ነፃ ያደርጋል የተባለ ዕቅድ ወጣ
በጎዳና ንግድ እየታመሱ የሚገኙ የአዲስ አበባ ከተማ ጎዳናዎችን ሥርዓት ለማስያዝ የከተማው ንግድ ቢሮ አዲስ ዕቅድ አወጣ፡፡
የንግድ ቢሮ ባወጣው አዲስ ዕቅድ መሠረት የጎዳና ነጋዴዎች በሚመደብላቸው ቦታ የንግድ ሥራቸውን ያካሂዳሉ፡፡ ይህን በማያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ደግሞ ዕርምጃ ይወስዳል፡፡
በድንበር አካባቢ የጠረፍ ንግድ ቢፈቀድም ቤንሻንጉል ጉምዝና ጋምቤላ ተጠቃሚ አይደለንም አሉ
ክልሎች ኢትዮጵያን ከሚያዋስኑ ጎረቤት አገሮች ጋር በ90 ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ የጠረፍ ንግድ እንዲያካሂዱ የፌዴራል መንግሥት ቢፈቅድም፣ በተለይ የቤንሻንጉል ጉምዝና የጋምቤላ ክልሎች ተጠቃሚዎች አይደለንም አሉ፡፡
የፌዴራል መንግሥት በጠረፍ አካባቢ የሚገኙ ክልሎች አገሪቱን ከሚያዋስኑ ክልሎች ጋር እንዲነግዱ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡ ነገር ግን በአንፃራዊነት ሶማሌ፣ አፋርና ቦረና አካባቢ የሚገኙ ሕዝቦች ከሶማሊያና ከሶማሌላንድ፣ ከጂቡቲና ከኬንያ ጋር በተሻለ ደረጃ እየተገበያዩ ነው፡፡
በፀጥታ መደፍረስ የተጎዳውን የንግድ እንቅስቃሴ የሚገመግም ጉባዔ ተጠራ
በአገሪቱ አጋጥሞ የነበረው የፀጥታ መደፍረስ በንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ ያሳደረውን ተፅዕኖ በመገምገም፣ መፍትሔ የሚያመላክት ጉባዔ በአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ በባህር ዳር ከተማ ሊካሄድ ነው፡፡
የንግድ ሚኒስቴር ከግንቦት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ቀናት በጠራው ‹‹የክልሎች መድረክ›› ጉባዔ ላይ፣ ዘጠኙ ክልሎችና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል፡፡
በቆራሊዮ አምሳል
‹‹አሮጌ ጫማ ብልቃጥ ጠርሙስ ቆርቆሮ ያለው›› የሚለውን ለየት ያለ ዘዬ ያለውን የቆራሊዮ ጥሪ ተከትለው ከበረንዳ ጫማ፣ ከመደርደሪያ ጠርሙስ፣ ከጓሮ መዘፍዘፊያና የብረት ቁርጥራጭ ይዘው የሮጡ ጥቂት አይደሉም፡፡ ቆራሊዮ የበርካቶች የልጅነት ትዝታም ጭምር ነው፡፡ የቅባት ጠርሙስ በ30 ሳንቲም ሸጠው ብስኩት ገዝተው የበሉ ብዙ ናቸው፡፡ አይጠቅሙም ተብለው የተጣሉ ቅራቅምቦዎች ሳይቀሩ ለቆራሊዮ ዋጋ አላቸው፡፡
Popular
በሕወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶና በሂደት ላይ የነበረው የወንጀል ክስ ተቋረጠ
በቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤ,(ዶ/ር)ና ባለፈው ሳምንት በተሾሙት...
[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]
ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው?
ምነው?
ምክር ቤቱም ሆነ...