Tuesday, March 28, 2023

Tag: አማራ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የተቀጠሩ ሠራተኞችን እመነጥራለሁ አለ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አጭበርብረው የተቀጠሩ ሠራተኞችን ለመመንጠር አዲስ ዕቅድ አወጣ፡፡ የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በሁሉም መሥሪያ ቤቶች ይህንን የሚሠራ ኮሚቴ ያቋቋመ ሲሆን፣ በማዕከል ደረጃ ፖሊስና ፍትሕ ቢሮ ያሉበት ግብረ ኃይል አቋቁሟል፡፡ ቢሮው ሒደቱ የሚመራበትን መመርያ በማዘጋጀት በማዕከል፣ በክፍለ ከተማና በወረዳ መዋቅሮች ከሚመለከታቸው ጋር ሲመክር ቆይቷል፡፡

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተሠራው የእንቦጭ መንቀያ ማሽን አጥጋቢ ሙከራ ማድረጉ ተገለጸ

በጣና ሐይቅ ላይ የተንሰራፋውን የእንቦጭ አረም ለመንቀል በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አማካይነት የተሠራው ማሽን አጥጋቢ ሙከራ ማድረጉ ታወቀ፡፡ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አማካይነት ማሽኑን ለመሥራት ሙከራ ሲደረግ ቆይቶ፣ ሰሞኑን በተደረገው ጥረት ማሽኑ አረሙን መንቀል እንደቻለ ታውቋል፡፡

በአማራ ክልል የመጀመርያው የመድኃኒት ፋብሪካ ሥራ ሊጀምር ነው

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረ ማርያም ወረዳ ቱለፋ ከተማ የተቋቋመው የመጀመርያው የመድኃኒት ፋብሪካ ሥራ ሊጀምር ነው፡፡ በቻይና ባለሀብቶች የተቋቋመውና ሒዩማን ዌል ፋርማሲዩቲካል በተሰኘው ድርጅት አማካይነት በአማራ ክልል ለመጀመርያ ጊዜ የተቋቋመው ‹‹ሒዩማን ዌል›› የተሰኘውና የመጀመርያ የሆነው የመድኃኒት ፋብሪካ፣ እሑድ ኅዳር 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ተመርቆ ሥራ እንደሚጀምር የአማራ ክልል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ይኼነው ዓለም ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

‹‹መንግሥት እንኳን የሰው ሕይወት ይቅርና የውሻ ደም መፍሰስ የለበትም ብሎ ነው እየሠራ ያለው›› ነገሪ  ሌንጮ (ዶ/ር)፣  የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች  ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ቅዳሜ ኅዳር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር፡፡ ኅዳር 29 ቀን 2010 ዓ.ም. የሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን፣ ስለህዳሴ ግድቡና አገሪቱ ስላለችበት የፀጥታ ሁኔታ የመግለጫቸው የትኩረት ነጥቦች ነበሩ፡፡

በኢትዮጵያ ግብርና ቀዳሚ የሆነው የጤፍ እርሻ በሜካናይዜሽን ሊደገፍ ነው

የግብርና ማሽኖችን ከቀረጥ ነፃ ለማስገባት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔ ይጠበቃል የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር ለአርሶ አደሩ አድካሚ ሆኖ የቆየውን የጤፍ እርሻ ሥራ በሜካናይዜሽን እንዲታገዝ ለማድረግ፣ ለመጀመርያ ጊዜ ጤፍ የሚያጭዱና የሚወቁ ማሽኖችን ከቻይና አስገባ፡፡

Popular

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...

Subscribe

spot_imgspot_img