Wednesday, May 29, 2024

Tag: ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ከኃላፊነታቸው ለቀቁ

የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመሆን በተሾሙት አቶ ፍፁም አረጋ ምትክ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን በሚያዝያ 2010 ዓ.ም. ተሹመው የነበሩት በላቸው መኩሪያ (ዶ/ር)፣ ከማክሰኞ መስከረም 2 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ  ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ፡፡

የውጭ የሎጂስቲክስ ኩባንያዎች የ49 በመቶ ድርሻ ይዘው እንዲገቡ ተፈቀደ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ብቻ ተከልሎ የቆየውን ዕቃዎችን የማሸግ፣ የማስተላለፍና የመርከብ ውክልና አገልግሎቶችን በመስጠት  መስክ ዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ኩባንያዎች ከ49 በመቶ በታች ያለውን አናሳ ድርሻ በመያዝ፣ ከአገር ውስጥ የሎጂስቲክስ ኩባንያዎች ጋር በሽርክና እንዲሠሩ ወሰነ፡፡

የኤምሬትስ ባለሀብቶች የጂማ ኢንዱስትሪ ፓርክን ሙሉ በሙሉ ለመረከብ ጠየቁ

የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ባለሀብቶች በጂማ ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን የኢንዱስትሪ ፓርክ ሙሉ በሙሉ ጠቅልለው ለመያዝ ጥያቄ ማቅረባቸውን፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ መንግሥትም ደስተኛ መሆኑን ገልጿል፡፡

የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ማበረታቻዎችን እንደሚከልስ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የአገሪቱን የኢንቨስትመንት አዋጅ በማሻሻል የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችን እንደሚከልስ አስታወቀ፡፡ የኢንቨስትመንት ኮሚሽነሩ በላቸው መኩሪያ (ዶ/ር) ከምክትሎቻቸው ጋር በመሆን ማክሰኞ ነሐሴ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ በኢንቨስትመንት አዋጁ ላይ ማሻሻያ ይደረጋል፡፡

የኢንቨስትመንት ኮሚሽነሩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተሾሙ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ላለፉት አምስት ዓመታት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ፍጹም አረጋ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተደርገው ተሾሙ፡፡ አቶ ፍጹም በአዲሱ ሥልጣናቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመሆን፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩን እንቅስቃሴዎች የመምራትና የማደራጀት ሥራዎችን የመወጣት ኃላፊነት እንደሚይዙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Popular

የኢትዮ ኤርትራ ሰሞነኛ ሁኔታና ቀጣናዊ ሥጋቱ

“ግንቡን እናፍርስ ድልድዩን እንገንባ” የሚል ፖለቲካዊ መፈክር ጎልቶ በሚሰማበት፣...

ኦሮሚያ ባንክ ከተበዳሪ ደንበኞቼ ውስጥ 92 በመቶ የሚሆኑት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ናቸው አለ

ኦሮሚያ ባንክ ለደንበኞቹ ከሰጠው ብድር ውስጥ ለአነስተኛና ለመካከለኛ ኢንተርፕራይዞች...

ሽቅብና ቁልቁል!

ጉዞ ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ ጀምረናል። ተሳፋሪዎች የዕለት ጉርሳቸውን መሸፈን...

እኛ ኢትዮጵያውያን ከየት መጥተን ወዴት እየሄድን ነው?

በአሰፋ አደፍርስ ኢትዮጵያውያን ከየትም እንምጣ ከየት እስከ 1445 ዓ.ም. እስላማዊና...

Subscribe

spot_imgspot_img