Tag: ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
የኮሮና ቫይረስን የመከላከል አቅም የሚጨምር መድኃኒት በኢትዮጵያ ማግኘት እንደተቻለ ተገለጸ
እ.ኤ.አ. በጃንዋሪ 2020 በቻይና ሁቤይ ግዛት ውሃን ከተማ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ከተገኘበት ጊዜ አንስቶ ዓለም ቫይረሱን ለመከላከያ፣ ለማከሚያና ለማዳኛ የሚሆኑ መድኃኒቶችን ለማግኘት እየተረባረበ ባለበት ወቅት፣ የጤና ሚኒስቴርና የኤኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በመቀናጀት ከባህላዊ መድኃኒት የተቀመመና የኮሮና ቫይረስን የመከላከል አቅም የሚጨምር ማከሚያ መድኃኒት ማግኘታቸውን አስታወቁ፡፡
ኢንተርኔት ሶሳይቲ የበይነ መረብ ጉባዔውን በአዲስ አበባ ማካሄድ ጀመረ
ኢንተርኔት ሶሳይቲ የተሰኘው ዓለም አቀፍ የበይነ መረብ ተቋም በኢትዮጵያ የመጀመርያውን የኢንተርኔት ልማት ኮንፈረንስ ከየካቲት 24 ቀን እስከ የካቲት 26 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ማካሄድ ጀምሯል፡፡
ኢትዮጵያ ያመጠቀቻት ሳተላይት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚኖራት ተገለጸ
እ.ኤ.አ. በጥቅምት 2015 በተፈረመ ስምምነት መሠረት ዕውን ሆና በቻይና መንግሥት በስምንት ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ዓርብ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ወደ ህዋ የመጠቀችው ሳተላይት፣ ለኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደምታስገኝ ተገለጸ፡፡
ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ሁለተኛዋ የኤሌክትሮኒክ ግብይት መድረክ የሚያደርጉ ስምምነቶች ተፈረሙ
በኢትዮጵያ ሰሞኑን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ባደረጉት ግዙፉ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ተቋም አሊባባ ግሩፕ ዋና ዳይሬክተር ቻይናዊው ጃክ ማ አማካይነት በኢትዮጵያ መንግሥትና በአሊባባ መካከል የተፈረሙ ሦስት ስምምነቶች፣ ኢትዮጵያ ከሩዋንዳ በመቀጠል በአፍሪካ የኤሌክትሮኒክስ ዓለም ግብይት መድረክ (Electronic World Trade Platform) ማዕከል እንድትሆን ያስችሏታል ተባለ፡፡
ኢትዮጵያ በአሥር ዓመታት የኑክሌር ኃይል ጥቅም ላይ ለማዋል ተዘጋጅታለች
ባለፈው ሳምንት በሩሲያ ሶቺ ከተማ በተካሄደው የሩሲያ አፍሪካ የኢኮኖሚ ፎረም ወቅት፣ ኢትዮጵያ የኑክሌር ኃይልን ለሰላማዊ ዓላማ ማዋል የምትችልበትን መበደኛ ስምምነት ከሩሲያ ጋር ተፈራረመች፡፡ የስምምነቱ መፈረም በመጪዎቹ አሥር ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ኑክሌርን ጥቅም ላይ ለማዋል ያስችላል ተብሏል፡፡
Popular
የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ
ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ
የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...
[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]
አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው?
ጠፋሁ አይደል?
ጠፋሁ ብቻ?!
ምን ላድርግ ብለሽ...
ኦሮሚያ ኢንሹራንስ በግሉ ኢንሹራንስ ዘርፍ ሁለተኛውን የገበያ ድርሻ ለመያዝ ያስቻለውን ውጤት ማስመዝገቡን ገለጸ
ኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ የባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት፣ የመለዋወጫ ዕቃዎች...