Saturday, April 20, 2024

Tag: ኤሌክትሪክ አገልግሎት

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቀጣይ በጀት ዓመት 25 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱን ተናገረ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2013 በጀት ዓመት ከ25 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ወደ ሥራ መግባቱን አስታወቀ፡፡ አገልግሎቱ በበጀት ዓመቱ አንድ ሚሊዮን ደንበኞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ማቀዱን ጠቁሞ፣ ከኤሌክትሪክ ፍጆታ 16.5 ቢሊዮን ብር፣ ከልዩ ልዩ ገቢዎች ስምንት ቢሊዮን ብርና ከአገልግሎት ክፍያ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር ለማግኘት በድምሩ 25 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ማቀዱግ ግልጽ አድርጓል፡፡

ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ተጨማሪ የውኃ ፍጆታ ሳይሆን የኤሌክትሪክ ኃይል መጥፋት አስቸግሮኛል አለ

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽ በኢትዮጵያ መከሰቱ ከተረጋገጠበት ጊዜ አንስቶ  በአዲስ አበባ ነዋሪዎች የውኃ አቅርቦት ችግር ይፈጠራል የሚል ሥጋት ቢኖርም፣ የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ግን እስካሁን ችግር የሆነበት የኤሌክትሪክ ኃይል መጥፋት እንጂ የውኃ ምርት እንዳልሆነ አስታወቀ፡፡

የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሜቴክ ብቸኛ አቅራቢነት እንዲያበቃ አደረገ

ከብሔራዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ብቻ የተለያዩ የኤሌክትሪክ መሣሪያዎች ሲረከብ የቆየው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአገር ውስጥ አምራቾች ተወዳድረው ምርታቸውን እንዲያቀርቡ ጋበዘ፡፡

የአሜሪካ ሞሮቶላ ኩባንያ ለኤሌክትሪክ አገልግሎት የሬዲዮ መገናኛ ቴክኖሎጂ አቀረበ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሞቶሮላ ሶሉሽንስ ከተሰኘው የአሜሪካ ኩባንያ ጋር በመተባበር ሠራተኞቹ መረጃ የሚለዋወጡበትና የደኅንነት ሥጋቶች የሚቀረፉበት እንዲሁም ለደንበኞቹም የተቀላጠፈ አገልግሎት ለማቅረብ ያስችላል ያለውን የሞባይል ሬዲዮ ግንኙነት ቴክኖሎጂ ግዥና የግንኙነት መስመር የመጀመርያ ምዕራፍ ተከላ ሥራ ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡  

 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቃሉን ባለመጠበቁ የሪል ስቴት ኩባንያው ደንበኞቼ ተጉላሉብኝ አለ

ኃይሌ ዓለም ኢንተርናሽናል ኩባንያ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አካባቢ ለገነባቸው ሪል ስቴት ቤቶች የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲገባለት ከዓመት በፊት ክፍያ ፈጽሞ ቢጠባበቅም፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቃሉን መጠበቅ ባለመቻሉ ደንበኞቹ እየተጉላሉበት መሆኑን አስታወቀ፡፡

Popular

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...

እጥረትና ውጥረት!

ጉዞ ከስድስት ኪሎ ወደ ቃሊቲ፡፡ ‹‹ይገርማል ቀኑ እንዴት ይሄዳል?››...

Subscribe

spot_imgspot_img