Tag: እሳት
በሞጣ ከተማ በቤተ እምነቶች ላይ የደረሰው ጥቃት እየተወገዘ ነው
በአማራ ክልል በምሥራቅ ጎጃም ዞን በሞጣ ከተማ ዓርብ ታኅሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ምሽት አንድ ሰዓት አካባቢ፣ በቤተ ክርስቲያንና በመስጊዶች ላይ የደረሰው የእሳት ቃጠሎ ጥቃት በመላ አገሪቱ እየተወገዘ ነው፡፡
ከ20 ሺሕ በላይ አባወራዎችን ሥጋት ላይ የሚጥል የጎርፍ አደጋ በአዲስ አበባ ሊከሰት ይችላል
በመጪዎቹ የክረምት ወራት በአዲስ አበባ ከተማ 169 ቦታዎች ለጎርፍ ሥጋት እንደሚጋለጡ፣ የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በአደጋው በአሥሩም ክፍላተ ከተሞች የሚገኙ ከ30 በላይ ወረዳዎች ተጋላጭ እንደሆኑ፣ 20,955 አባወራዎችም የጉዳት ሰለባ ሊሆኑ እንደሚችሉ ለሪፖርተር የገለጹት፣ የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ናቸው፡፡
በአንዋር መስጊድ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ በርካታ መደብሮች ወደሙ
መርካቶ በአንዋር መስጊድ በከለላቸው የንግድ መደብሮች ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ንብረት መውደሙን የንብረቶቹ ባለቤቶች ገለጹ፡፡
የአንዋር መስጊድ አስተዳደር ካከራያቸው 300 ያህል መደብሮች ውስጥ 50 ያህሉ መቃጠላቸውን የተገለጸ ቢሆንም፣ ንብረቶቻቸው የእሳቱ ሰለባ የሆኑባቸው ባለንብረቶች ግን የሱቆቹ ብዛት ከ163 በላይ መሆናቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ለአምስት ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያሠራጭ ማከፋፈያ ማዕከል የእሳት አደጋ ደረሰበት
ከአዲስ አበባ በ245 ኪሎ ሜትር ላይ በጅማና በሰኮሩ ከተሞች መካከል በሚገኘው፣ ሰኮሩ በመባል በሚታወቀው ለአምስት ከተሞች ኤሌክትሪክ ኃይል የሚያሠራጭ ኃይል ማከፋፈያ ማዕከል ላይ የእሳት አደጋ ደረሰበት፡፡
ሰሜን ሸዋ ውስጥ በ43 ቤቶች ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ሁለት ሰዎች ሞቱ
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሚዳ ኦሮሞ ወረዳ እምቢበሎ ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ በ43 ቤቶች ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ሁለት ሰዎች ሞቱ፡፡ ሦስት ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
Popular