Tag: እሳት
በሸካ ደን በተነሳ ሰደድ እሳት በ200 ሔክታር ላይ የሚገኝ የተፈጥሮ ሀብት ወደመ
በደቡብ ክልል ሸካ ዞን ዓርብ መጋቢት 7 ቀን 2010 ዓ.ም. የተነሳ ሰደድ እሳት፣ 200 ሔክታር በሚገመት መሬት ላይ የሚገኝ የተፈጥሮ ደን አወደመ፡፡
በሳምንቱ ዓርብ መጋቢት 14 ቀን 2010 ዓ.ም. ሰደድ እሳቱ ወደ አጎራባች አካባቢዎች መዛመቱ የተገታ ቢሆንም፣ ሙሉ በሙሉ ግን አለመጥፋቱ ታውቋል፡፡
በምዕራብ ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ክልል ኢሊባቦራ ዞን ጎሬ ከተማ ወደ ደቡብ ክልል ሸካ ዞን ማሻ ከተማ በሚወስደው መንገድ 14 ኪሎ ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኝ ተፈጥሯዊ ደንና ውኃ አዘል መሬት ላይ ሰደድ እሳቱ ተከስቷል፡፡
Popular