Tag: እናት ባንክ
እናት ባንክ ከምርት ገበያው ጋር ለመሥራት 16ኛ ባንክ ሆነ
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አብረውት የሚሠሩትን ባንኮች ቁጥር 16 ማድረሱን አስታወቀ፡፡ ምርት ገበያው ባለፈው ሐሙስ ታኅሳስ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ከእናት ባንክ ጋር ባደረገው ስምምነት ላይ እንደተገለጸው፣ እናት ባንክ ከምርት ገበያው ጋር በመሥራት 16ኛው ባንክ በመሆን ዘመናዊ የግብይት ሥርዓቱን ተቀላቅሏል፡፡
የኮሜሳ ንግድና ልማት ባንክ ለላኪዎች የብድር ዋስትና የሚሰጥ ስምምነት ከእናት ባንክ ጋር ተፈራረመ
የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ አገሮች የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) የንግድና የልማት ባንክ በወጪ ንግድ መስክ ለሚሠማሩ አነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች የብድር ዋስትና ለመስጠት የመግባቢያ ስምምነት ከእናት ባንክ ጋር ተፈራርሟል፡፡
እናት ባንክ 216 ሚሊዮን ብር አተረፈ
እናት ባንክ በ2010 የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት ያገኘው የትርፍ መጠን በ47 በመቶ ወይም በ60 ሚሊዮን ብር በማሳደግ 216 ሚሊዮን ብር ማድረሱን ገለጸ፡፡
ባንኩ ባለፈው ቅዳሜ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ይፋ ባደረገው ዓመታዊ የሒሳብ ሪፖርት በ2010 የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት የተመዘገበው ትርፍ በባንኩ ታሪክ ከፍተኛው የትርፍ ዕድገት መጠን የተመዘገበበት እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡
እናት ባንክ 216 ሚሊዮን ብር አተረፈ
እናት ባንክ በ2010 የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት ያገኘው የትርፍ መጠን በ47 በመቶ በማሳደግ 216 ሚሊዮን ብር ማድረሱን ገለጸ፡፡
የእናት ባንክ መሥራቿ መዓዛ ሽኝት
የእናት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ የነበሩትና ከሁለት ሳምንት በፊት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በመሆን የተሾሙት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ፣ በእናት ባንክ ለነበራቸው ቆይታ ዕውቅና ለመስጠትና ለአዲሱ ሹመታቸውም የባንኩ ማኅበረሰብ የእንኳን ደስ አለዎ ምኞቱን ለመግለጽ፣ ሐሙስ ኅዳር 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ምሽት በኢሊሊ ሆቴል ግብዣ ተሰናድቶ ነበር፡፡
Popular