Thursday, March 30, 2023

Tag: እናት ባንክ

ተሰናባቹ የእናት ባንክ ቦርድና አዲሱ አመራር ርክክብ ፈጸሙ

እናት ባንክን ለማቋቋም መንቀሳቀስ የጀመሩት መሥራቾች ውጥናቸው የተጀመረው ከአሥር ዓመታት በፊት ነበር፡፡ በአሥር እንስቶች ዋና አደራጅነትም ባንኩን የማቋቋም ሥራ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ ለባንኩ ምሥረታ የሚያስፈልገው 75 ሚሊዮን ብር በአክሲዮን ሽያጭ አማካይነት ከተሟላ በኋላ፣ ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ አግኝቶ ባንኩ ሥራ ከጀመረ ስድስተኛ ዓመቱን ይዟል፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን እናት ባንክን በስድስት ሚሊዮን ብር ዕዳ ከሰሰ

እናት ባንክ አክሲዮን ማኅበር ሳትኮን ኮንስትራክሽን ለተባለ የሥራ ተቋራጭ የገባውን ዋስትና በተደጋጋሚ እንዲከፍል ሲጠየቅ ሊከፍል ባለመቻሉ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የስድስት ሚሊዮን ብር የፍትሐ ብሔር ክስ መሠረተበት፡፡ ባለሥልጣኑ በእናት ባንክ አክሲዮን ማኅበር ላይ ክሱን ሊመሠርት የቻለው፣ ከሰመራ-ዲዲግሳ ከሚያሠራው የመንገድ ግንባታ ጋር በተገናኘ በገባው ዋስትና ምክንያት ነው፡፡

እናት ባንክ ሁለተኛዋን የቦርድ ሰብሳቢ ሰየመ

በ11 ሴቶች መሥራችነት የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማጎልበት የተነሳው እናት ባንክ፣ በቅርቡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተቀባይነት ካገኙት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ውስጥ ወ/ሮ ሀና ጥላሁንን የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ በማድረግ መረጠ፡፡ እናት ባንክ ከተመሠረተ ጀምሮ ወ/ሮ ሀና ለባንኩ ሁለተኛዋ ከፍተኛ ኃላፊ ለመሆን በቅተዋል፡፡ 

ብሔራዊ ባንክ የእናትና የብርሃን ባንክ ዕጩ የቦርድ አባላትን አፀደቀ

አዳዲስ የቦርድ አባላትን በመሰየም እንዲያፀድቅላቸው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ካቀረቡ ባንኮች መካከል እናት ባንክ ያቀረባቸው ዕጩዎች በቦርድ አባልነት እንዲያገለግሉ የገዥውን ይሁንታ በማግኘቱ፣ በወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ሲመራ የቆየው ቦርድ ለአዲሱ ተተኪ ኃላፊነቱን ማስረከቡ ተገለጸ፡፡ ብርሃን ባንክ ያካሄደው የአዲስ ቦርድ አባላት ምርጫም በብሔራዊ ባንክ ፀድቆለታል፡፡

የእናት ባንክ መሥራቿ ወ/ሮ መዓዛ የቦርድ ኃላፊነታቸውን አስረከቡ  

ከመደበኛው የባንክ አገልግሎት በተጓዳኝ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማጎልበት፣ ለሥራዎቻቸውም ተገቢውን ፋይናንስ ለማቅረብ ታስቦ የተቋቋመው እናት ባንክን ከምሥረታው ጀምሮ በአደራጅነትና በቦርድ ሰብሳቢነት ሲያገለግሉ የቆዩት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ኃላፊነታቸውን አስረክበዋል፡፡

Popular

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...

አይ የእኛ ነገር!

የዛሬው ጉዞ ከጀሞ ወደ ፒያሳ ነው፡፡ መንገዱ ለሥራ በሚጣደፉ፣...

የዓለም ኢኮኖሚ መናጋት ለወቅታዊው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ነው?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባለፈው ማክሰኞ መጋቢት 16...

የተዘነጋው የከተሞች ሥራ የመፍጠር ተልዕኮ

በንጉሥ ወዳጅነው አሁን አሁን የአገራችን የሥራ ዕድል ፈጠራ ጉዳይ አንገብጋቢና...

Subscribe

spot_imgspot_img