Tuesday, February 27, 2024

Tag: ኦዴፓ

ኢዜማ የኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ የተላለፈውን መልዕክት ተቃወመ

የሰላም የይቅርታና የምሥጋና በዓል የሆነው ኢሬቻን የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) አደረጃጀት መጥለፉ ሳያንሰው የተለመደውን የ100/150 ዓመት የሰባሪ/ተሰባሪ ትርክት ማቀንቀኑ አገሪቱን ወደ አንድነት ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት ወደ ኋላ የሚጎትትና የሚበርዝ በመሆኑ እንዲህ ዓይነቱ ትርክት በአስቸኳይ እንዲታረም የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) ጠየቀ፡፡

እስክንድር ነጋ ሊሰጠው የነበረው መግለጫ ኦዴፓ ባደራጃቸው ቄሮዎች መስተጓጎሉን ተናገረ

ከሁለት ሳምንታት በፊት በተፈጸመው ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ግድያ ምክንያት የታሰሩ ሰዎችን በሚመለከት ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት በቢሮው ውስጥ በዝግጅት ላይ እያለ፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ያደራጃቸው ቄሮዎች በፈጠሩት ረብሻ ምክንያት መስተጓጎሉን እስንክድር ነጋ ገለጸ፡፡

አብን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጭምር የፈረሙበት የፖለቲካ ፓርቲዎች የቃል ኪዳን ሰነድ እየተጣሰ ነው አለ

በምርጫ ቦርድ የተመዘገቡና ሕጋዊ መሆናቸው የተረጋገጠ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና ኦዴፓን ወክለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጭምር የፈረሙበት የቃል ኪዳን ሰነድ እየተጣሰ ነው ሲል፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አስታወቀ፡፡

የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ

ነባሩን የሕወሓት አመራር አባል አቶ ብርሃነ ኪዳነ ማርያምን ከሁለት ዓመት በፊት በመተካት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሸን (ኢቢሲ) ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ሥዩም መኮንን፣ ማክሰኞ ግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ.ም. ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ለሠራተኞች አስታወቁ፡፡

ኦነግ ጦላይ ማሠልጠኛ የገባው ጦር ያጋጠመው የምግብ መመረዝ እንዲጣራ ጠየቀ

ጦላይ ወታደራዊ ማሠልጠኛ የገባው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ያጋጠመው ጦር የምግብ መመረዝ ተጣርቶ ለሕዝብ ይፋ እንዲደረግ ኦነግ ጠየቀ፡፡ የኦነግ ጦር አባላት እሑድ ሚያዝያ 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ማለዳ ቁርስ ላይ ሻይ ሲጠጡ በመመረዛቸው ምክንያት የሆድ ቁርጠትና ትውከት እንዳጋጠማቸው ታውቋል፡፡ በወሊሶ ከተማም ሕክምና የተደረገላቸው ሲሆን፣ ከሕመም በስተቀር ሌላ የከፋ ጉዳት አለመድረሱ ተገልጿል፡፡

Popular

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...

ሕወሓት በትግራይ ጦርነት ወቅት በፌዴራል መንግሥት ተይዘው ከነበሩት አባላቱ መካከል ሁለቱን አሰናበተ

በሕወሓት አባላት ላይ የዓቃቤ ሕግ ምስክር የነበሩት ወ/ሮ ኬሪያ...

የኤሌክትሪክ ኃይል ለታንዛኒያ ለመሸጥ የሚያስችል ስምምነት ለመፈጸም የመንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ለማከናወን የሚያስችለውን...

Subscribe

spot_imgspot_img