Tag: ዓለም ባንክ
በመተማመኛ ሰነድ ክፍያ መዘግየት የውጭ ባንኮች በአገር ውስጥ ባንኮች ላይ እምነት እያጡ ነው
በኢትዮጵያ ለዓመታት በዘለቀው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ሳቢያ፣ የአገር ውስጥ ባንኮች አስመጪዎችን በመወከል የሚልኩት ባንክ መተማመኛ ሰነድ ወይም ሌተር ኦፍ ክሬዲት በወቅቱ ክፍያ መፈጸም ባለመቻላቸው በርካታ ባንኮች ከኢትዮጵያ ባንኮች ጋር የመሥራት ፍላጎትና እምነት እያጡ መምጣታቸው እየተነገረ ነው፡፡
የዓለም ባንክ ለበጀት ድጋፍ የሚውል የ250 ሚሊዮን ዶላር ብድርና ዕርዳታ ፈቀደ
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የበጀት ድጋፍ የሚውል የ250 ሚሊዮን ዶላር ብድርና ዕርዳታ በመፍቀድ ከመንግሥት ጋር ስምምነት ፈረመ፡፡ ከዚህ ገንዘብ ውስጥ ግማሹ በዕርዳታ መልክ እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡
መንግሥት ከዓለም ባንክ ጋር የ16 ቢሊዮን ብር ብድርና ዕርዳታ ስምምነት ተፈራረመ
ገንዘብ ሚኒስቴርና የዓለም ባንክ ለሁለተኛው የዕድገትና የተወዳዳሪነት ፕሮግራም የሚውል የልማት ፋይናንስ ፖሊሲ ማስፈጸሚያ የ500 ሚሊዮን ዶላር ወይም የ16 ቢሊዮን ብር ብድርና ዕርዳታ ተፈራረሙ፡፡
ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የውኃ አሞላልና አለቃቅን በተመለከተ የራሷን ሰነድ ለድርድር ልታቀርብ ነው
የኢትዮጵያ መንግሥት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የውኃ አሞላልና አለቃቀቅን የተመለከተ ሰነድ አዘጋጅቶ ለድርድር እንደሚያቀርብ ተሰማ። አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የሪፖርተር ምንጭ እንደገለጹት፣ በአሜሪካና በዓለም ባንክ አመቻችነት የግድቡን የውኃ አሞላልና አለቃቀቅን በተመለከተ ሲደረግ የቆየው ድርድር ውጤት የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጎዳ በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን የአገሪቱን ሉዓላዊነትና ጥቅም የሚያስከብር የድርድር ሰነድ እንዲያዘጋጅ በመንግሥት ታዞ ሰነዱን በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
በዓለም ባንክ የንግድ ሥራ ምቹነት መመዘኛዎች ከ50 በላይ ደረጃዎችን ለማሻሸል ማቀዱን መንግሥት አስታወቀ
የዓለም ባንክ ግሩፕ ለዓመታት ይፋ ሲያደርገው በቆየውና ከ190 ያላነሱ አገሮችን የንግድ ሥራ ምቹነት ከባቢያዊ ሁኔታን በሚመዝንበት ሪፖርቱ፣ ኢትዮጵያ ከ150ዎቹ ግርጌ ስትመደብ ቆይታለች፡፡ በቅርቡ ይፋ በተደረገው የባንኩ ‹‹ኢዝ ኦፍ ዱዊንግ ቢዝነስ 2020›› ሪፖርትም ከ190 የኢትዮጵያ ደረጃ 159ኛ ላይ አስቀምጧታል፡፡
Popular
ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች
በበቀለ ሹሜ
ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...
‹‹መንግሥት ለአገር ውስጥ የኅትመት ኢንዱስትሪ ገበያ ከመፍጠር ጀምሮ ሥራ የመስጠት ኃላፊነት አለበት›› አቶ ዘውዱ ጥላሁን፣ የኢትዮጵያ አሳታሚዎችና አታሚዎች ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ
የኅትመት መሣሪያ በጉተምበርግ ከተፈበረከ ከ400 ዓመታት በኋላ በኢትዮጵያ በ1863...
በሲሚንቶ ፋብሪካ ላይ የታየው ተሞክሮ በሌሎች ምርቶች ላይም ይስፋፋ!
ሰሞኑን በኢትዮጵም ሆነ በአፍሪካ ደረጃ ግዙፍ ስለመሆኑ የተነገረለትን የለሚ...