Tag: የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ
በግማሽ ዓመቱ የመንግሥት ተቋማት ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ አተረፉ
በመንግሥት ይዞታ ሥር የሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት በ2012 ግማሽ ዓመት ከታክስ በፊት 10.7 ቢሊዮን ብር እንዳተረፉ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክም ከኪሳራ ወጥቷል ተብሏል፡፡
በሩብ ዓመቱ አትራፊ ከተባሉ የልማት ድርጅቶች ሜቴክ 42 ሚሊዮን ብር በማትረፍ ከዋናዎቹ ተርታ ተመደበ
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በሥሩ ከሚያስዳድራቸው መካከል በማኑፋክቸሪንግ መስክ ከአምስቱ ድርጅቶች፣ በሩብ በጀት ዓመቱ 41.76 ሚሊዮን ብር ትርፍ በማስመዝገብ አትራፊ ከተባሉ ድርጅቶች የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ከቀዳሚዎቹ ተርታ እንደተሠለፈ ኤጀንሲው ይፋ ተደረገ፡፡
12 የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወደ ግል ሊዛወሩ ነው
መንግሥት በ2012 በጀት ዓመት 12 የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ለማዛወር ዕቅድ መያዙንና በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ያለውን የ70 በመቶ የባለቤትነት ድርሻም ለመሸጥ ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከዕቅዱ በላይ 850 ሚሊዮን ብር ገቢ ማስገኘቱ ተገለጸ
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በሥሩ የሚተዳደሩ የልማት ድርጅቶችን የ2011 ዓ.ም. አፈጻጸም መገምገም መጀመሩን አስመልክቶ ሰሞኑን ከተመለከታቸው መካከል፣ ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በሽያጭም በገቢም ከዕቅዱ በላይ በማስመዝገብ ከ850 ሚሊዮን ብር በላይ ማስገኘቱን አስታወቀ፡፡
መንግሥት በቆርኪና ጣሳ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ላይ የነበረውን ሙሉ ይዞታ በ130 ሚሊዮን ብር ሸጦ ወጣ
መንግሥት በኢትዮጵያ ቆርኪና ጣሳ ማምረቻ ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር ላይ የነበረውን የ75 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ በ130 ሚሊዮን ብር በመሸጥ ሙሉ ለሙሉ ይዞታውን ለግል ኩባንያ አስረከበ፡፡
Popular
በሕገ መንግሥቱ የተዋቀረው ‹‹የብሔር ፖለቲካ›› እና ‹‹ሥርዓቱ›› ያስከተለው መዘዝና መፍትሔው
(ክፍል አራት)
በዓቢዩ ብርሌ (ጌራ)
ባለፈው ጽሑፌ (በክፍል ሦስት) አሁን ያለው...
ለመጪው ዓመት የሚያስፈልገው 4.3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነዳጅ 4.4 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይጠይቃል
ለመጪው 2016 ዓ.ም. ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ለታቀደው 4.3...