Tag: የማዕድን ሚኒስቴር
መንግሥት ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያላቸው የድንጋይ ከሰል ማዕድን ፕሮጀክቶችን ስምምነት አፀደቀ
ዜና
አማኑኤል ይልቃል -
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታኅሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው ሦስተኛ መደበኛ ስብሰባው፣ በስምንት አገር በቀል ኩባንያዎች የተያዙና በድምሩ ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያላቸው ስምንት የከሰል ማዕድን ፕሮጀክት ስምምነቶችን አፀደቀ፡፡
ሁለት ቢሊዮን ዶላር ማስተማመኛ ካፒታል እንዲያስቀምጥ የታዘዘው የቻይና ኩባንያ ትዕዛዙን እንዳልፈጸመ ታወቀ
በሶማሌ ክልል የተገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ ለማልማት ፈቃድ ያገኘው የቻይና ኩባንያ፣ ፕሮጀክቱን ለማከናወን የሚያስችል የፋይናንስ አቅም ያለው መሆኑን ሁለት ቢሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት ካፒታል ተቀማጭ በማድረግ እንዲያረጋግጥ በመንግሥት ቢታዘዝም፣ ትዕዛዙን እንዳልፈጸመ ታወቀ።
መንግሥት የድንጋይ ከሰልን ከውጭ ማስገባት እንዲቆም ውሳኔ ማሳለፉ ታወቀ
የማዕድን ሚኒስቴር የድንጋይ ከሰል ከውጭ ማስገባት እንዲቆም ውሳኔ ማሳለፉ ታወቀ፡፡ በአገር ውስጥ ለሚመረቱ የተለያዩ ዓይነት የድንጋይ ከሰል ምርቶች፣ እንደ ጥራት ደረጃቸው ዝቅተኛ የመሸጫ መነሻ ዋጋ ትመና ለማድረግ ዝግጅት ላይ መሆኑም ተገልጿል፡፡
የማዕድን ሚኒስቴር በአዲሱ ተልዕኮው ኢንዱስትሪዎችን ለማጎልበት ትኩረት እንደሚሰጥ አስታወቀ
የአገሪቱን ዕምቅ የማዕድን ሀብት ከመለየትና ጥቅም ላይ እንዲውሉ ከማድረግ ባለፈ የማዕድን ኢንዱስትሪ ዘርፍን በልዩ ሁኔታ ለመገንባት ትኩረት በመስጠት፣ የብረታ ብረት፣ ሲሚንቶ፣ የአፈር ማዳበሪያና የግንባታ ግብዓት ኢንዱስትሪዎችን ልማት ለማጎልበት ትኩረት እንደሚሰጥ የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሶማሌ ክልል የተገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ ልማት ያዘገየው የቻይና ኩባንያ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ማስተማመኛ እንዲያቀርብ ታዘዘ
በሶማሌ ክልል የተገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ አልምቶ ኤክስፖርት ለማድረግ፣ በማዕድን ሚኒስቴር ፈቃድ የተሰጠው የቻይናው ኩባንያ ፖሊ ጂሲኤል፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ልማቱን ማካሄድ የሚችል መሆኑን ሁለት ቢሊዮን ዶላር ብሔራዊ ባንክ በማስቀመጥ እንዲያረጋግጥ በመንግሥት ታዘዘ።
Popular