Thursday, June 13, 2024

Tag: የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ

የአፍሪካ አገሮች የአፍሪካ የባህር ትራንስፖርት ቻርተር ማፅደቅ እንዳለባቸው ተገለጸ

የአፍሪካ አገሮች በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የተዘጋጀውን የአፍሪካ የባህር ትራንስፖርት ቻርተርን ማፅደቅ እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡ ይህ የተገለጸው በቅርቡ በኢኳቶሪያል ጊኒ መዲና ማላቦ በተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የመሠረተ ልማት ፕሮግራም ጉባዔ ላይ ነው፡፡ በጉባዔው የተካፈሉት የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሮባ መገርሳ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የመሠረተ ልማት ፕሮግራም ያዘጋጀው የአፍሪካ የባህር ትራንስፖርት ቻርተር ለአፍሪካ አገሮች የሚያስገኘው በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡

ከ3.2 ሚሊዮን ቶን በላይ ስንዴና ማዳበሪያ በኢትዮጵያ መርከቦች እንደሚጓጓዝ ይጠበቃል

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የ2011 ዓ.ም. አፈጻጸሙን እንዲሁም የ2012 በጀት ዓመት ዕቅዱን በተመለከተ ባለፈው ሳምንት መግለጫ በሰጠበት ወቅት፣ በየጊዜው እየተስፋፋ ስለመጣው የወጪ ንግድ የጭነት አገልግሎትም አብራርቶ ነበር፡፡

በሃያ አንድ ዓመቱ የተቀጨው ሕንፃ

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሲገለገልበት የቆየው ለገሃር አካባቢ የሚገኘው ባለ አራትና ሰባት ወለል ሕንፃ፣ እንደ ብዙዎቹ የአዲስ አበባ የዕድሜ እኩዮቹ በአገልግሎት ዘመኑ ልክ ባለበት ቦታ ለመቆየት ያልታደለ ሆኗል፡፡

ኢትዮጵያ የምፅዋን ወደብ በቅርቡ መጠቀም እንድትጀምር የሚያስችል ዝግጅት በመደረግ ላይ ነው

ኢትዮጵያና ኤርትራ በቅርቡ በመሀላቸው ሰላም ካሰፈኑ በኋላ የምፅዋ ወደብ ለኢትዮጵያ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል በመሆኑ፣ አገልግሎቱን ለመጀመር በሁለቱም መንግሥታት በኩል ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው፡፡

የግል ትራንስፖርት ኩባንያዎች በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት እንዲሰማሩ ጥያቄ ቀረበ

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የግል የትራንስፖርት ኩባንያዎች፣ በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት እንዲሳተፉ ጥያቄ አቀረበ፡፡ የሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከማሪታይም ባለሥልጣን ጋር በጋራ በመሆን ባደረጉት ጥናት፣ በጂቡቲ ወደብ ለበርካታ ቀናት ተከማችተው የሚቆዩ የአገሪቱ ንብረቶች በፍጥነት መነሳት አለባቸው፡፡ በኮንቴይነር ታሽገው ከሚቀርቡ ንብረቶች ውጪ ያሉ ሌሎች ዕቃዎችም በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት ወደ አገር ውስጥ መግባት እንዳለበት ተስማምተዋል፡፡

Popular

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...

የ‹‹ክብር ዶክትሬት›› ዲግሪ ጉዳይ

በንጉሥ ወዳጅነው ‹‹የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ግልጽ የሆነ መመርያ እስኪወጣ ድረስ...

Subscribe

spot_imgspot_img