Tag: የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ከእስር ተለቀቁ
ዓቃቤ ሕግ በመንግሥት ላይ ጉዳት በማድረስ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ተጠርጥረው የታሰሩትን አቶ ሳምሶን ወንድሙንና አቶ በቀለ ባልቻን ከእስር ለቀቀ፡፡ ዓቃቤ ሕግ ግን ፍርድ ቤቱን ሳያስፈቅድ ግለሰቦቹን በመልቀቁ፣ ፍርድ ቤቱ ድርጊቱን ተቃውሞታል፡፡
የመንገዶች ባለሥልጣን ኃላፊዎች ከሁለት ደረጃ አንድ ሥራ ተቋራጮች ጋር ክስ ተመሠረተባቸው
ለሁለቱም ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ያላግባብ ክፍያ መፈጸሙ ተገልጿል
ሳትኮንና ሀዚ አይአይ ሥራ ተቋራጮች በክሱ ተካተዋል
ከሐምሌ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ ሲካሄድባቸው በከረሙት በኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሰባት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ በገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ገምሹ በየነ (በሌሉበት) እና በዲኤምሲ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል ማሞ (በሌሉበት) ላይ ዓርብ መስከረም 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተ፡፡
በኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ላይ ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ አማካሪ ታሰሩ
በሚኒስቴሩና በባለሥልጣኑ ከፍተኛ ኃላፊዎች ላይ ምርመራ ተጠናቀቀ
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ ያላግባብ ክፍያ እንዲፈጸም በማድረግ የተጠረጠሩና በፓን አፍሪካ ድርጅት ውስጥ አማካሪ የሆኑ ግለሰብ፣ በቁጥጥር ሥር ውለው ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡
Popular