Tag: የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ
በዘረፋ ሥጋት በትግራይ ክልል የሚገኙ የባንክ ቅርንጫፎች እንደተዘጉ ነው
የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ካደረሰ ጀምሮ በፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት ቡድን መካከል የሕግ ማስከበር ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን ተከትሎ፣ በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ የባንክ ቅርንጫፎች ላይ የዝርፊያ ምልክቶች በመታየታቸው ተዘግተው እንዲቆዩ የብሔራዊ ባንክ አሳሰበ፡፡
የባንኮች የሚሰበስቡት ተመላሽ የብድር መጠን እየቀነሰ መምጣቱ አሳሳቢ መሆኑ ተገለጸ
የአገሪቱ ባንኮች እየሰበሰቡ ያሉት የተመላሽ ብድር መጠን እየቀነሰ መምጣቱንና ባንኮቹ በዘንድሮው የመጀመርያ ሩብ ዓመት ያሰባሰቡት ተመላሽ ብድር በ15 በመቶ እንደቀነሰ ተገለጸ፡፡
ባንኮች ካፒታላቸውን ማሳደግ ወይም መዋሀድ ግድ እንደሚላቸው ተጠቆመ
በአገሪቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የግል ባንኮች በዚህ ዓመት ካፒታላቸውን ማሳደግ እንደሚጠበቅባቸውና ለዚህም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ እንደሚያወጣ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ካፒታሉን ለማሳደግ ግን የተለያዩ አማራጮች እንደሚታዩ ተጠቆመ፡፡
ከ13 ዓመታት ፈታኝ ምጥ በኋላ የተወለደው ዘምዘም ባንክ
በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ እንደ አዲስ ታሪክ ሊቆጠር የሚችለው፣ በኢትዮጵያ የመጀመርያው ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ ባንክ አገልግሎት በይፋ ሥራ መጀመሩን ሊያረጋግጥለት የሚችል የዕውቅና የፈቃድ ሰርቲፊኬት፣ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለዘምዘም ባንክ ተሰጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ አዲሱን የብር ኖት ማሠራጨቱን ተናገረ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነባሩን በአዲሱ ብር ለመተካት እየተካሄደ ባለው እንቅስቃሴ፣ ከ90.4 ቢሊዮን ብር በላይ አዲሱን ብር ማሠራጨቱንና በአገሪቱ ከሚገኝ አንድ ቅርንጫፍ ውጪ ለ6,561 ቅርንጫፎች መድረሱን አስታውቋል፡፡
Popular