Tag: የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ሳይንስ ኢንስቲትዩት
በኢትዮጵያ እስከ ሐምሌ 17 ቀን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 12,693 ሆኗል
የጤና ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አስመልክቶ፣ ሐምሌ 17 ቀን 2012 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫው እንዳስታወቀው፣ በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 7,264 የላቦራቶሪ ምርመራ 760 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፣ የሦስት ሰዎች ሕይወትም አልፏል፡፡
በኢትዮጵያ እስከ ሐምሌ 14 ቀን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 11,072 ሆኗል
የጤና ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አስመልክቶ፣ ሐምሌ 14 ቀን 2012 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫው እንዳስታወቀው፣ በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6,544 የላቦራቶሪ ምርመራ 561 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን፣ የሰባት ሰዎች ሕይወትም አልፏል፡፡
በኢትዮጵያ እስከ ሐምሌ 10 ቀን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 9,147 ሆኗል
የጤና ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አስመልክቶ፣ ሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫው እንዳስታወቀው፣ በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 7,407 የላቦራቶሪ ምርመራ 344 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን፣ የ13 ሰዎች ሕይወትም አልፏል፡፡
በአራት ቀናት ውስጥ የ22 ሰዎች ሕይወት አልፏል
የጤና ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አስመልክቶ፣ ካለፈው ቅዳሜ ሐምሌ 4 ቀን እስከ ማክሰኞ ሐምሌ 7 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ የነበረውን ገጽታ በሰጠው መግለጫው እንዳስታወቀው በአራቱ የ22 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡
“ከኮሮና ቫይረስ ተጠበቁ”
ኮቪድ-19 በወረርሽነት ዓለምን ካካለለ መንፈቅ አልፎታል፡፡ ባለፉት ስድስት ወራት ሕዝበ ዓለም ከኮሮና ቫይረስ እንዲጠበቅ፣ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ እንዳይዝ የጤና ባለሙያዎችና ዓለም አቀፋዊም ሆነ አገራዊ ተቋማት ማስገንዘቢያዎችን ከመስጠት ችላ ያሉበት ጊዜ አልነበረም፡፡
Popular