Tag: የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ
ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለቶኪዮ 2020 ዝግጅት ጀመረ
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ‹‹ተደረገም አልተደረገም›› በሚል ከስድስት ወራት በፊት ተዋቅሮ የነበረው ብሔራዊ ዝግጅት ኮሚቴ ቀደም ሲል ባቀደው መሠረት ሥራ እንዲጀምር ማድረጉን አስታወቀ፡፡ በወቅቱ ከተቋቋመው ብሔራዊ ዝግጅት ኮሚቴው መካከል ከተለያዩ የጤና ተቋማት ተዋቅሮ የነበረው የሕክምና ኮሚቴ ባለፈው ዓርብ ዕቅዱን ይፋ አድርጓል፡፡
ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለብሔራዊ ፌዴሬሽኖች 1.6 ሚሊዮን ብር ደገፈ
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለተፈጠረው ችግር የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለብሔራዊ ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽኖች 1.6 ሚሊዮን ብር፣ እንዲሁም ለአንጋፋ አትሌቶች ደግሞ 200 ሺሕ ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡
ኦሊምፒክ ኮሚቴ አትሌቶችን እንደሚደግፍ አስታወቀ
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ከውድድር ውጪ ለሆኑ ብሔራዊ አትሌቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡ በሌላ በኩል ወርልድ አትሌቲክስ ወረርሽኙን ተከትሎ ውድድር ለተቋረጠባቸው ፕሮፌሽናል አትሌቶች የገንዘብ ድጋፍ አደርጋለሁ ብሏል፡፡
ኦሊምፒክ ኮሚቴና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ ስፖርት ኮሚሽን አሳሰበ
የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዝግጅት ከመጀመሩ አስቀድሞ በከፍተኛ አለመግባባት ውስጥ ሆነው የዘለቁት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ ስፖርት ኮሚሽን አሳስቧል፡፡ ከሰሞኑ ከቶኪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅት ጋር ተያይዞ አለመግባባቱ አፍጥጦ መውጣቱ ብዙዎችን አነጋግሯል፡፡
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ዝግጅት ይቀጥላል ተባለ
ዓለም በኮሮና ቫይረስ እየደረሰባት ያለው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት፣ የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በተያዘለት መርሐ ግብር መሠረት ይካሄዳል ማለቱ ተገለጸ፡፡
Popular