Tag: የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ
የኦሊምፒክ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት በተመራጭ እንዲመራ ተወሰነ
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሰሞኑን ባደረገው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጽሕፈት ቤቱ በተመራጭ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንዲመራ የሚደነግግ ደንብ ማፅደቁ ታወቀ፡፡ የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ በመሆን ሲያስተዳድሩ የቆዩት አቶ ታምራት በቀለ ከነበሩበት ደረጃ ዝቅ ብለው በምክትል ኃላፊነት እንዲያገለግሉ መወሰኑ ተነግሯል፡፡
መንግሥት ለአትሌቶች ሽልማት የመደበው 22 ሚሊዮን ብር የገባበት አልታወቀም
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በ12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ ተሳትፎን ከዝግጅት ምዕራፍ እስከ ውጤት የነበረውን የተመለከተ ሪፖርት አቀረበ፡፡ በዕለቱ በጨዋታዎቹ ተሳትፎ የነበራቸውን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው ብሔራዊ ፌዴሬሽኖችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተው የቀረበውን ሪፖርት ገምግመዋል፡፡
የተግባር ክትትልና ቁጥጥር የሚሻው የስፖርቱ ዘርፍ ብሔራዊ ስሜቱን ማደስ ጀምሯል
በአልጀሪያ በተካሔደው ሦስተኛው የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ፣ ከተሳተፈባቸው ስድስት ስፖርቶች በሦስቱ 25 ሜዳሊያዎችን አስመዝግቦ ተመልሷል፡፡
Popular