Tag: የዓለም ዋንጫ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ በፊፋ ወርኃዊ የአገሮች ደረጃ ከነበረበት አሽቆለቆለ
የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) በዚህ ወር ይፋ ባደረገው የአገሮች እግር ኳስ ደረጃ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ባለፈው ወር ከነበረበት ሦስት ደረጃዎችን አሽቆልቁሏል፡፡
ዋሊያዎቹ የዓለም ዋንጫ በምድብ ሁለት ማጣሪያ ጨዋታ ዚምባቡዌን ረቱ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) በዓለም ዋንጫ የምድብ ሁለት ማጣሪያ ጨዋታ ዚምባቡዌን አሸነፈች፡፡ በሚቀጥለው ዓመት በኳታር ለሚዘጋጀው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታቸውን እያደረጉ የሚገኙት ዋሊያዎቹ ለድል የበቁት በመጠናቀቂያ ሰዓት ላይ የተገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት አስቻለው ታመነ በማስቆጠሩ ነው፡፡
ዋሊያዎቹ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያውን ጨዋታን ከነገ በስቲያ ያከናውናሉ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ለ2022 ኳታር ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን አርብ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጋና ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደርጋል፡፡ የብሔራዊ ቡድኑ 23 ተጫዋቾች የዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታቸውን ለማድረግ ማክሰኞ ነሐሴ 25 ቀን ወደ ስፍራው አቅንቷል፡፡
ዋሊያዎቹና የዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል
የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) እ.ኤ.አ. በ2022 ኳታር ለምታዘጋጀው የዓለም ዋንጫ የተሳታፊ አገሮች ምድብ ድልድልን ይፋ ጥር 11 ቀን 2012 ዓ.ም. አድርጓል፡፡ ኢትዮጵያ ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ጠንካራ የእግር ኳስ አገር ጋና፣ ደቡብ አፍሪካና ዚምባቡዌ በሚገኙበት ምድብ መደልደሏ ታውቋል፡፡
መፍትሔ የሚሻው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጎል ድርቅ
በኢንስትራክተር አብርሃም መብርሃቱ የሚሠለጥነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) ስብስብ እስካሁን በምሥራቅ አፍሪካ በደካማነቷ ከምትጠቀሰው ጅቡቲ በስተቀር በሌሎች አገሮች ላይ የሚስተዋልበት ጎል የማስቆጠር ክፍተት፤ ባለፈው ረቡዕ ነሐሴ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. ለ2022 ኳታር የዓለም ዋንጫ የመጀመርያ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የሌሶቶ አቻውን በባህር ዳር ስታዲየም አስተናግዶ ጨዋታውን ያለ ጎል በአቻ ውጤት ማጠናቀቁ ማረጋገጫ ሆኗል፡፡
Popular
መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...
በሰጥቶ መቀበል መርህ መደራደርና ሰላም ማስፈን ለምን ያቅታል?
በያሲን ባህሩ
አገር ግንባታ የትውልድን ትልቅና ታሪካዊ ኃላፊነት የሚጠይቅ ተግባር...