Tuesday, March 28, 2023

Tag: የፌዴሬሽን ምክር ቤት    

እየተካረረ የመጣው የፌዴራል መንግሥትና የትግራይ ክልላዊ መንግሥት እሰጥ አገባ አቅጣጫ

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከረረና እየተባባሰ የመጣው የፌዴራል መንግሥትና የትግራይ ክልላዊ መንግሥት እሰጥ አገባ፣ አሁን ተግባራዊ ፍጥጫዎችን ማሳየት ጀምሯል፡፡ የሁለቱ ወገኖች ፍትጊያ የጀመረው በሐዋሳ ከተካሄደው የመጨረሻው የኢሕአዴግ ጉባዔ ጀምሮ የፓርቲውን ርዕዮተ ዓለም ለመቀየርና ግንባሩን ወደ አንድ ውህድ ፓርቲ ለመቀየር የተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ቢሆንም፣ በተለይ ሕወሓት ብልፅግና ፓርቲ ተብሎ የተመሠረተው ፓርቲ ውስጥ ላለመሳተፍ ከወሰነ ወዲህ መካረሩ ጦዟል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል መንግሥት ላይ ውሳኔ አሳለፈ

የፌዴራል መንግሥት ከትግራይ ክልል መንግሥት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳያደርግ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ምክር ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው ነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. አድርጎት በነበረው አስቸኳይ ጉባዔ፣ በትግራይ ክልል የሚካሄደው ምርጫ እንዳልተደረገና እንደማይፀና ያስተላለፈው ውሳኔ ተጥሶ በማግኘቱ መሆኑን ትናንት ማምሻውን በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን አሳውቋል፡፡

‹‹ወይ ሁላችንም በዴሞክራሲያዊ መንገድ እንሄዳለን ወይም ማናችንም አንሄድም›› ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

በ2012 ዓ.ም. መካሄድ የነበረበት ጠቅላላ ምርጫ በኮሮና ወረርሽኝ መከሰት ምክንያት ሊካሄድ ባለመቻሉ የአምስት ዓመት የሥልጣን ዘመናቸው እንዲራዘም ከተደረገው የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ተጨማሪ፣ የሥራ ዘመናቸውን በጋራ ስብሰባ በጀመሩበት ወቅት የተገኙት የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር የሕግ የበላይነትን ማስከበር መንግሥት ዘንድሮ ትኩረት የሚያደርግበት ዓብይ አጀንዳ መሆኑን አስታወቁ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እንዲመሠረት የቀረበው ጥያቄ በሕዝበ ውሳኔ እንዲረጋገጥ ተወሰነ

በደቡብ ክልል ሥር የነበሩ ስድስት ብሔሮች በጋራ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ለመመሥረት በምክር ቤቶቻቸው የወሰኑትን ውሳኔ ተከትሎ፣ ማክሰኞ መስከረም 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ስብሰባውን ያደረገው ፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕዝበ ውሳኔ እንዲረጋገጥ ወሰነ፡፡

ሕወሓት በፌዴራል መንግሥት ውስጥ የሚሠሩና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላቱ ኃላፊነታቸውን እንዲለቁ ጥሪ አደረገ

ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ  እንዲራዘም በመደረጉ ምክንያት ከመስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም. በኋላ የፌዴራል መንግሥት ሥልጣን እንደሚያበቃና ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆኑ ፓርላማው ሕጋዊ ሥልጣን እንደሌላቸው ያስታወቀው ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት)፣ በፌዴራል መንግሥት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ያላቸውን ውክልናና ኃላፊነት ለቀው ሪፖርት እንዲያደርጉ አደረገ፡፡

Popular

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...

Subscribe

spot_imgspot_img