Thursday, March 30, 2023

Tag: ዶፒንግ

ማራቶን ሯጯ እታፈራሁ ተመስገን የ12 ዓመት ቅጣት ተላለፈባት

የማራቶን ሯጯ እታፈራሁ ተመስገን፣ በስፖርት የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን በመጠቀምና ሰነዶችን በማጭበርበር ተደርሶባት ከማንኛውም ውድድር 12 ዓመት ቅጣት እንደተላለፈባት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ አበረታች ቅመሞች ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡ ጽሕፈት ቤቱ የአትሌቷ ጥፋት በወንጀል ጭምር የሚያስጠይቅ መሆን አለመሆኑ እየተጣራ ይገኛል ብሏል፡፡

አትሌት ወንድ ወሰን ከተማ በዶፒንግ ምክንያት አራት ዓመት ታገደ

አትሌት ወንድወሰን ከተማ የተከለከለ የስፖርት አበረታች ቅመም (ዶፒንግ) መጠቀሙ በመረጋገጡ ከማንኛውም የአትሌቲክስ ውድድር ለአራት ዓመት መታገዱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ አበረታች ቅመሞች ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡ ጽሕፈት ቤቱ ተጨማሪ የሁለት አትሌቶች ጉዳይ በመጣራት ላይ መሆኑንም ገልጿል፡፡

የኦሊምፒክ ዝግጅት የአትሌቶችን ሐሳብ ያካተተ እንደሚሆን ተገለጸ

ከመጪው ሐምሌ አጋማሽ ጀምሮ በጃፓን በተለያዩ ከተሞች እንደሚከናወን የሚጠበቀው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በውድድሩ ወቅት በአገሪቱ የሚኖረው የአየር ፀባይ በራሱ ኢትዮጵያውያኑን ጨምሮ ለብዙ አትሌቶች አስቸጋሪ መሆኑ እንደማይቀር የዘርፉ ሙያተኞች ይናገራሉ፡፡

ሩሲያ ከስፖርታዊ ውድድሮች የአራት ዓመት እገዳ ተጣለባት

የዓለም አቀፍ የፀረ አበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ) ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ (ዋዳ) ሩሲያን በማንኛውም ስፖርታዊ ውድድሮች እንዳትሳተፍ የአራት ዓመት እገዳ መጣሉን አስታወቀ፡፡ ተቋሙ በተለይ በአትሌቲክሱ ከፍተኛ የሆነ ቁጥጥርና ክትትል ከሚያደርግባቸው አገሮች አንዷ እንደሆነች የሚነገርላት ኢትዮጵያ ከሩሲያ ትልቅ ትምህርት ልትወስድ ይገባል የሚሉ አሉ፡፡

አትሌቲክሱና አበረታች ቅመሞች

ኢትዮጵያ በዓለም የውድድር መድረኮች ከምትወከልባቸው ስፖርቶች አትሌቲክስ በዋናነት ይጠቀሳል፡፡ ይሁንና ስፖርቱ አሁን አሁን የአገሮችን ስምና ዝና ከፍ እንዲል ከማስቻሉ ጎን ለጎን ለተወዳዳሪዎቹ የሚሰጠው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ከፍ እያለ መምጣቱን ተከትሎ፣ አትሌቶች አሸናፊ ለመሆን በሚያደርጉት ጥረት ተጨማሪ ኃይል የሚጠቀሙበት ዕድል እየሰፋ መምጣቱ አሳሳቢ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡

Popular

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...

አይ የእኛ ነገር!

የዛሬው ጉዞ ከጀሞ ወደ ፒያሳ ነው፡፡ መንገዱ ለሥራ በሚጣደፉ፣...

የዓለም ኢኮኖሚ መናጋት ለወቅታዊው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ነው?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባለፈው ማክሰኞ መጋቢት 16...

የተዘነጋው የከተሞች ሥራ የመፍጠር ተልዕኮ

በንጉሥ ወዳጅነው አሁን አሁን የአገራችን የሥራ ዕድል ፈጠራ ጉዳይ አንገብጋቢና...

Subscribe

spot_imgspot_img