Tag: ጎርፍ
በጎርፍ አደጋ 42,306 ቤተሰቦች ተፈናቀሉ
በሰባት ክልሎች በ38 ወረዳዎች በደረሱ የጎርፍ አደጋዎች 42,306 ቤተሰቦች ከቀዬአቸው መፈናቀላቸውን፣ የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ከ20 ሺሕ በላይ አባወራዎችን ሥጋት ላይ የሚጥል የጎርፍ አደጋ በአዲስ አበባ ሊከሰት ይችላል
በመጪዎቹ የክረምት ወራት በአዲስ አበባ ከተማ 169 ቦታዎች ለጎርፍ ሥጋት እንደሚጋለጡ፣ የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በአደጋው በአሥሩም ክፍላተ ከተሞች የሚገኙ ከ30 በላይ ወረዳዎች ተጋላጭ እንደሆኑ፣ 20,955 አባወራዎችም የጉዳት ሰለባ ሊሆኑ እንደሚችሉ ለሪፖርተር የገለጹት፣ የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ናቸው፡፡
በሶማሌ ክልል በጎርፍ ምክንያት 98 ሺሕ ሰዎች ተፈናቀሉ
በሚያዝያ ወር በተደረገ ጥናት በሶማሌ ክልል በሸበሌ ዞን 165 ሺሕ የሚጠጉ ዜጎች በጎርፍ መጠቃታቸውን፣ ከእነዚህም ውስጥ 98 ሺሕ ያህል ሰዎች ከቀዬአቸው መፈናቀላቸው ተገለጸ፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ በዚህ ሳምንት በወጣው ሳምንታዊ ሪፖርት፣ በክልሉ በተከሰተው ጎርፍ ሁለት ወረዳዎች ውስጥ አምስት ሺሕ ቤቶች መውደማቸውን፣ በሸበሌ ዞን የሚገኙ 72 ትምህርት ቤቶችና 63 የጤና ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱን አስታውቋል፡፡
Popular