Tag: ጦርነት
ሰላማዊ ሰዎችን ሰለባ ያደረገው የአፍጋን ታሊባን ጦርነት
በአፍጋኒስታን ከ20 ዓመታት በፊት በመንግሥትና በታሊባን ታጣቂዎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ሰበብ በማድረግ በአገሪቷ ከትመው የነበሩት አሜሪካና የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ወታደሮች አፍጋኒስታንን ወደ ሰላም መመለስ አልቻሉም፡፡
ከአሜሪካ የአሸባሪዎች መዝገብ የተፋቀው የየመን ሁቲ ቡድን
የመን የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ከተዘፈቀች ስድስት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ እነዚህ ዓመታት በተለይ ሴቶች፣ ሕፃናትና አረጋውያን ፍዳን የቆጠሩበት ነው፡፡ የእርስ በርስ ግጭት ለየመን ብርቅ ባይሆንም፣ ጦርነቱ የለየለት የሳዑዲ መራሹ ጦር እ.ኤ.አ. በ2015 ጣልቃ ሲገባ ነበር፡፡
ከሰይፍ እንራቅ!
አገር አስከፊ ወደ ሆነው ግጭት ገብታለች፡፡ ነገሮች ወደ ግጭት እንዳያመሩ አነሰም በዛ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ ጥረቶች ውጤት ሊያጡ ባለመቻላቸው ይኸው የጥይት ድምፅ መሰማት ጀምሯል፡፡ በጥቂቶች እምቢተኝነት ወንድሞች መተላለቃቸው ያሳዝናል፡፡
ታላቁን የዓድዋ ድል ስንዘክር ለኢትዮጵያ ትንሳዔ ተምሳሌት እናድርገው!
ኢትዮጵያ በዓለም የተመሰከረላት ታሪካዊ አገር ስለመሆኗ ከዋነኛ ቅርሶቿና ከታላላቅ ታሪካዊ ክንውኖቿ መካከል አንዱ፣ የዛሬ 124 ዓመት በዘመኑ በአውሮፓ ኃያል ከነበሩት ኮሎኒያሊስቶች ተርታ ከሚታወቀውና እስከ አፍንጫው ድረስ ዘመናዊ የጦር መሣሪያ ከታጠቀው የዘመኑ የጣሊያን ዘመናዊ ወራሪ ጦር ጋር ተዋግታ፣ ዓለምን ጉድ ያሰኘውን የዓድዋ አንፀባራቂ ድል መጎናፀፏ ነው፡፡
አፍሪካውያን ሕፃናት በውትድርና
በተፈጥሮ ሀብት የበለፀገች አህጉር ነች፡፡ ሀብት የለገሳት ብትሆንም፣ ሀብቷን ለመጠቀም አልታደለችም፡፡ በተለይ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገሮች አንዴ በቸነፈር ሲመቱ አንዴ በጦርነት ሲታመሱ ዓመታትን ዘልቀዋል፡፡ የጤና ቀውስም የቀጣናው መለያ ነው፡፡ ከዚህ እኩል በየአገሮቹ የሚነሱ ግጭቶች አፍሪካ ከድህነት አረንቋ እንዳትወጣ ምክንያት ሆነዋል፡፡
Popular