Tag: ፌዴሬሽን
ክልሎች የዕጩዎቻቸውን ሰብዕናና ብቃት እንዲያጤኑ ተጠየቀ
ገላጋይ ሕግ አጥቶ ለወራት ሲያወዛግብ የቆየው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ ለመጨረሻ ጊዜ በተባለለት ግንቦት 26 ቀን 2010 ዓ.ም. በአፋር ሰመራ ይደረጋል፡፡ ክልሎች ለምርጫው ዕጩ የሚያቀርቡበት ቀነ ገደብ ከነገ በስቲያ ዓርብ ግንቦት 10 ቀን ያበቃል፡፡
ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በቅርቡ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አከናውኖ፣ ምርጫውን በሚመለከት ተፈጥሮ የቆየውን ብዥታ እንዲጠራ በማድረግ፣ አዲስ የአስመራጭ ኮሚቴ መሰየሙ አይዘነጋም፡፡
የእግር ኳሱ ጉባዔ ስያሜውን የሚመጥን ውሳኔ እንዲያሳልፍ ተጠየቀ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዓለም አቀፍ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (ፊፋ) የተላከውን የምርጫ ሕግ ለማፅደቅ ለቅዳሜ ሚያዝያ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. በካፒታል ሆቴል ጠቅላላ ጉባዔውን ጠርቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ጠቅላላ ጉባዔው ፊፋ ባስተላለፈው ትዕዛዝ መሠረት ቀጣዩን የፌዴሬሽኑን ፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለመምረጥ የሚያስችለውን አዲስ አስመራጭ ኮሚቴ እንደሚሰየም ይጠበቃል፡፡
የአዲሱ አስመራጭ ኮሚቴ ምርጫና ከጉባዔው የሚጠበቀው
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቀጣይ አመራርን ለመምረጥ እየተደረገ የነበረው የተንዛዛ አካሄድ ምንም እንኳ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) መፍትሔ ያለውን የውሳኔ ሐሳብ ቢያሳልፍም፣ አሁንም መቋጫውን አላገኘም፡፡ በተለያዩ ግለሰባዊ ፍላጎቶች ፍትጊያዎችን ያስተናገደው ይህ ምርጫ ከበርካታ ባለሙያዎችና አስተያየት ሰጪዎች የሰላ ትችት ሲያስተናግድ ከርሟል፡፡
የፊፋ መልዕክተኞችና ትዝብት ውስጥ የገባው የእግር ኳሱ ምርጫ
ከሰሞኑ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ተወካዮች በአዲስ አበባ ቆይታ አድርገው፣ የአገሪቱን የስፖርት አመራሮችና ዕጩ ተወዳዳሪዎችን አነጋግረው ተመልሰዋል፡፡ ተወካዮቹ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑን ቀጣይ አመራሮች ለመምረጥ በነበረው ሒደት ሲከናወን የቆየውንና ያለውን ሽኩቻ ተከትሎ ለማጣራት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣ ከተነገረ ሰነባብቷል፡፡
የእግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች ምርጫ ለአራተኛ ጊዜ ተራዘመ
የሥራ ዘመኑን በፈጸመው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴና ፕሬዚዳንት ምትክ ምርጫ ለማካሄድ ለየካቲት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ተቀጥሮ የነበረው ጉባዔ ለአራተኛ ጊዜ ተራዘመ፡፡
Popular
[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]
አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...